1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃዋሚው ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቄ ተከለከልኩ ሲል መንግሥትን ወቀሰ።

እሑድ፣ መስከረም 28 2010

የፓርቲ አመራር አባል የሆኑት አቶ አበበ አካሉ እንዳሉት በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሔድ የቀረበው ጥያቄ ከከተማው መሥተዳድር አዎንታዊ ምላሽ ተነፍጎታል።

https://p.dw.com/p/2lOiN
Äthiopien Addis Abeba Pressekonferenz Parteien
ምስል DW/G. T. Hailegiorgis

ሰማያዊ ፓርቲ ለሰልፍ ፈቃድ አላገኘም

ተቃዋሚው ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቄ ተከለከልኩ ሲል መንግሥትን ወቀሰ። የፓርቲ አመራር አባል የሆኑት አቶ አበበ አካሉ እንዳሉት በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሔድ የቀረበው ጥያቄ ከከተማው መሥተዳድር አዎንታዊ ምላሽ ተነፍጎታል። ፓርቲው ፈቃድ ከልክሎኛል ያለውን ሊሞግት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ መመሥረቱንም አቶ አበበ አክለው ገልጠዋል። የአዲስ አበባ መስተዳድር በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።