1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰሜን ኮርያና ቢል ክሊንተን

ረቡዕ፣ ሐምሌ 29 2001

ከወራት በፊት ሰሜን ኮርያ ድንበር ተሻግራችሁ ገብታችኋል ያለቻቸዉን የአሜሪካ ዜግነት ያላቸዉን ሁለት ሴት ጋዜጠኞች ማሰሯን ይታወሳል። ፍርድም ተሰጥቷል።

https://p.dw.com/p/J4HY
ክሊንተንና የተፈቱት ጋዜጠኞችምስል AP

የታሳሪዎቹ ጉዳይ ሲያነጋግር ከርሞ ትናንት ወደፒዮንግያንግ ያቀኑት የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ቢል ክሊንተን ጋዜጠኞቹን አስፈትተዉ ይዘዉ ወደአገራቸዉ መመለስ ተሳክቶላቸዋል። የኦባማ አስተዳደር የቢል ክሊንተን ጉዞ በግል የተደረገ ተልዕኮ ነዉ ከማለት ሌላ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።

አበበ ፈለቀ/ሸዋዬ ለገሠ/ ተክሌ የኋላ