1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት ቀጥሏል፤ መኢአድ

ሰኞ፣ ጥር 27 2005

በተለይ በጉራፈርዳ የሚፈናቀለዉ አርሶአደር ቁጥር ከዕለት ወደእለት እየጨመረ መሄዱን በመዘርዘር ገበሬዉ ከነልጆቹ ለጎዳና ህይወት መዳረጉን አመልክቷል። ታጣቂዎች አርሶአደሩን አፈናቅለዉ መሬቱን እንደሚቀራመቱ መረጃ እንደደረሰዉ ያመለከተዉ የመኢአድ መግለጫ የሰዉ ህይወት ያለፈበት አጋጣሚ መኖሩንም ጠቅሷል።

https://p.dw.com/p/17XjQ
Die Gambia Street und Churchill Avenue führen schnurgerade auf das Rathaus der äthiopischen Hauptstadt Addis Abeba. Aufnahme vom Januar 2007. Foto: Peter Smolka +++(c) dpa - Report+++
ምስል picture alliance/dpa


የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ የስልጣን እድሜን ለማራዘም የሚፈፀመዉ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ስጠት ቀጥሏል ሲል መግለጫ ይፋ አደረገ። ድርጅቱ በመግለጫዉ በተለይ በጉራፈርዳ የሚፈናቀለዉ አርሶአደር ቁጥር ከዕለት ወደእለት እየጨመረ መሄዱን በመዘርዘር ገበሬዉ ከነልጆቹ ለጎዳና ህይወት መዳረጉን አመልክቷል። ታጣቂዎች አርሶአደሩን አፈናቅለዉ መሬቱን እንደሚቀራመቱ መረጃ እንደደረሰዉ ያመለከተዉ የመኢአድ መግለጫ የሰዉ ህይወት ያለፈበት አጋጣሚ መኖሩንም ጠቅሷል። ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ የድርጅቱን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝደንት አነጋግሮ ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ዮርጊስ

ሸዋዮ ለገሠ

ሂሩት መለሰ