1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሱዳን በሃገርዋ የሚገኙ ስደተኞችን መመለስ መጀመርዋ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 23 2008

የሱዳን መንግሥት በሃገሪቱ የሚገኙትን ሥደተኞች ያለፈቃዳቸው ወደየአገራቸዉ እየመለሰ መሆኑ ተመለከተ። አንዳንድ የዉጭ መገናኛዎች እንደዘገቡት፣ የሱዳን መንግሥት ይህን ርምጃ መዉሰድ የጀመረዉ ስደተኞች ወደ አዉሮጳ እንዳይሻገሩ ከአዉሮጳ መንግሥታት ጋር በደረሰው ውል መሠረት መሆኑ ነው።

https://p.dw.com/p/1Ixm8
Karte Ethiopia und Eritrea ENG

[No title]

እስካሁን፣ በሱዳን ይኖሩ የነበሩ ወደ 900 የሚሆኑ ኤርትራዉያን በሱዳን መንግሥት አስገዳጅነት ተመልሰዋል፣ ሌሎች 400 ኤርትራዉያን ታስረዋል።
ይህንን የሱዳን ርምጃ የመብት ተሟጋቹ «ሂውመን ራይትስ ዎች» በጥብቅ ተቃዉሞታል። ሱዳን በሃገርዋ የሚገኙ አፍሪቃዉያን ስደተኞችን ወደየሃገራቸዉ መመለስ ጀምራለች ስለመባሉ በኬንያ የሚገኘዉን ወኪላችንን በስልክ ጠይቀነው ነበር።

ፋሲል ግርማ

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ