1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳውዲ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ሁኔታ 

እሑድ፣ ሰኔ 25 2009

የሳውዲ ዐረቢያ መንግሥት በሀገሩ የሚገኙ ሕጋዊ የመኖሪያ እና የሥራ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ ዜጎች በዘጠና ቀናት ውስጥ ሀገሩን ካላንዳች ቅጣት ለቀው እንዲወጡ ባለፈው መጋቢት 29/03/2017 ያወጣውና ከጥቂት ቀናት በፊት ቀነ ገደቡ የተጠናቀቀውን አዋጅ ባለፈው ሐሙስ ለአንድ ወር ማራዘሙ ተሰምቷል።  

https://p.dw.com/p/2fjWT
Saudi-Arabien Regierung verlängert Deadline für illegale Migranten aus Äthiopien um einen Monat
ምስል DW/S. Shibru

ሳውዲ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ሁኔታ 

በሳውዲ ዐረቢያ አሉ ከሚባሉት ከሁለት ሚልዮን የሚበልጡት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ከሌላቸው መካከል፣ ብዙዎቹ ከአፍሪቃ እና እስያ ሃገራት የሄዱ የውጭ ዜጎች ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያውያኑ ቁጥር ከ400,000 በላይ መሆኑ ይገመታል። እስካሁን የተመለሱት ግን በቁጥር ሲታይ ንዑስ ነው። 42,000 ገደማ ብቻ ነው። ወደ ሀገር የመመለሱ ሂደት፣ እንዲሁም፣ አሁንም በሳውዲ ዐረቢያ  የሚገኙት ለመመለስ ተዘጋጅተው በመጠባበቅ ላይ ያሉት እና ገና ውሳኔ ላይ ያልደረሱት ሕጋዊ የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ የሌላቸው ወገኖች ሁሉ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፣ ከፍተኛ ችግርም አጋጥሟቸዋል። አሳሳቢው የእነዚህ ዜጎች ጉዳይ እና የወደፊቱ እጣቸው ምን ሊሆን ይችላል? ውይይት አካሂደንበትል።  

አርያም ተክሌ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ