1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳዑዲ ሕገወጥ ለተባሉ የውጭ ዜጎች ምህረት ማወጇ

ረቡዕ፣ መጋቢት 13 2009

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በሀገሪቱ በሕገወጥ መንገድ የሚኖሩ የዉጭ ዜጎችን ያለምንም ቅጣት እና እንግልት ከግዛቱ እንዲወጡ የሚያስችል የምህረት አዋጅ አወጣ፡፡ ለዘጠና ቀናት እንደሚቆይ የተገለጸው የምህረት አዋጅ “ ከህገወጥነት የነጻች ሀገር ” ወይንም A Nation without violation የሚል መጠሪያ ተስቶታል፡፡

https://p.dw.com/p/2ZkMv
Äthiopische Rückkehrer aus Saudi Arabien
ምስል DW/S. Shibru

MMT_Beri. Riyad (Saudi amnesty illegal expatriate ) - MP3-Stereo

 የምህረት አዋጁ የሀገሪቱ ንጉሥ እና የሁለቱ ቅዱሳን መስጊዶች የበላይ ጠባቂ በሆኑት ንጉሥ ሰልማን አብዱል አዚዚ ፍቃድ አግኝቷል፡፡ አልጋ ወራሹ እና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትሩ ልዑል መሀመድ ቢን ናይፍ በሳዑዲ በሕገወጥነት የሚኖር የማንኛውም ሀገር ዜጋ ከሀገሪቱ በቀላሉ እና በሰላማዊ መንገድ እንዲወጣ የተመቻቸለትን መንገድ ሊጠቀምበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ ከሪያድ ዘጋቢያችን ስለሺ ሽብሩ ዘገባ ልኮልናል።

ስለሺ ሽብሩ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ