1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳዑዲ አረቢያ የታሰሩ ኢትዮጵዉያን

ሐሙስ፣ የካቲት 8 2004

የሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት ያሰሯቸዉን ኢትዮጵዉያን ክርስቲያኖች እስልምና እንዲቀበሉ ግፊት እያደረጉባቸዉ ነዉ ሲል አንድ የክርስቲያኖች መብት ተማጋች ድርጅት ወቀሰ።እስረኞች ግን ሐይማኖታቸዉን እንዲቀይሩ ተደረገባቸዉ ሥለተባለዉ ተፅዕኖ ያወሱት ነገር የለም

https://p.dw.com/p/144Vk
ምስል Fotolia/Scanrail


የሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣናት የሐገሪቱን ሕግና ሥርዓት ጥሰዋል በሚል ወንጀል ያሰሯቸዉን ኢትዮጵዉያን ክርስቲያኖች እስልምና እንዲቀበሉ ግፊት እያደረጉባቸዉ ነዉ ሲል አንድ የክርስቲያኖች መብት ተማጋች ድርጅት ወቀሰ።ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘዉ ዓለም አቀፍ የክስቲያን መብት አስከባሪ የተሰኘዉ ተቋም እስረኞቹ ለማስፈታት የፊታችን ማክሰኞ ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ ሰልፍ ጠርቷል።የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የሐይማኖት ኮሚሽን የተሰኘዉ ድርጅት በበኩሉ ኢትዮጵያዉያኑ እስረኞች አንድም እንዲፈቱ አለያም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ጠይቋል።አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

 የእስረኞቹ ሁኔታ

የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ያነጋገራቸዉ እስረኞች ግን ሐይማኖታቸዉን እንዲቀይሩ ተደረገባቸዉ ሥለተባለዉ ተፅዕኖና ጫና ያወሱት ነገር የለም።ይሁንና እስረኞቹ የነሱንም ሆነ የሌሎች ኢትዮጵያዉን እስረኞችን ችግር ለማቃለል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሥልጣናት ብዙም አልጣሩም በማለት ይወቅሳሉ።የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካዮች ግን ወቀሳዉን አይቀበሉትም።ዝር ዝሩን እነሆ።

አበበ ፈለቀ

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ