1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳይንስ፤ ሥ/ቴክኒክና ፈጠራ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 10 2004

ተፈጥሮ ያደለው ፣ የደለበ ጥሬ ሀብት እያለው ፣ በልማት ፣ ከሁሉም ክፍላተ ዓለም መጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሚነገርለት አፍሪቃ፣ ለዕድገቱ ዋናው አንቀሳቃሽ ሞተር፤ ትምህርት ፣ በተለይም ሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ፣ ከዚህም ጋር የተያያዘው

https://p.dw.com/p/14ft1
2 ኬንያውያት ናይሮቢ ውስጥ በአንድ «ኢንተርኔት ካፌ»ምስል AP

የፈጠራ ውጤት መሆኑን ከተገነዘበ ውሎ አድሯል። በመሆኑም፤ የተፈጥሮ ሳይንስና ሂሳብ ፣ በከፍተኛ ደረጃ የሚቀሰምባቸው ተቋማትን ለማስፋፋት ካለ እቅድና ጥረት ባሻገር፤ ዕድገትን ማፋጠን ስለሚቻልበት ሁኔታ መመከሩ አልቀረም። ይሁንና በሳይንስና ሥነ ቴክኒክ እንዲሁም የፈጠራ ወጤት ላይ አፍሪቃውያን አንድ መድረክ ፈጥረው ሲመክሩ ፤ በቅርቡ በናይሮቢ ፤ ኬንያ ፣ የተካሄደው በዓይነቱ የመጀመሪያው መሆኑ ነው የተነገረው።

ከክፍለ ዓለሙ 4 ማዕዘናት የተሰባሰቡ፣ የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ጠበብት እንዲሁም የየሀገራቱ የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ሚንስትሮች፤ ናይሮቢ ውስጥ ከመጋቢት 21 እስከ 23,2004 ፣ የ 3 ቀናት ጉባዔ ማካሄዳቸው ታውቋል። ኢትዮጵያን በመወከል በጉባዔው ተገኝተው ከነበሩት መካከል፣ የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ፣ ሚንስትር ደኤታ፣ አቶ መሐሙዳ ጋዝ ይገኙበታል። ከእንዲያ ዓይነቱ፣ የሳይንስና ሥነ ቴክኒክ ጉባዔ፣ በአጠቃላይ ለአፍሪቃው ክፍለ ዓለም፣ በተናጠልም ኢትዮጵያን ለመሳሰሉ ሀገራት የሚቀሰመው ጠቃሚ ጉዳይ ምን ይሆን? ክቡር ሚንስትሩን ጠይቄአቸው ነበር---

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ