ሴራልዮን እና ደም ያፋሰሰው አልማዝዋ
ሰኞ፣ ነሐሴ 3 2002ማስታወቂያ
አልማዝ ፣ በርካታ የሴራልዮን ዜጎችን ያስፈጀው ፣ ለ 11ዓመት ዓመታት የተካሄደው ጦርነት ዋነኛ የገንዘብ ምንጭ ሆኖ አገልግሏል ። ከአማፅያኑ አልማዝ ወስደው በምትኩ አማፅያንን መሳሪያ በማስታጠቅ ክስ የተመሰረተባቸው የዚያን ጊዜው የላይቤሪያ መሪ ቻርልስ ቴይለር ጉዳይ ዴን ሀግ በሚገኘው ዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት እየታየ ነው ። የዶይቼቬለ ባልደረባ Alexander Göbel እንደዘገበው የሴራልዮን ጦርነት ካበቃ ዓመታት ቢቆጠሩም የሴራልዮን ህዝብ ግን አሁንም የአልማዝ ሀብቱ ተጠቃሚ አይደለም ።
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ