1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለደቡብ ሱዳን የተመድ እና የአፍሪቃ ህብረት ምክክር

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 3 2008

ሰላም የራቃትን ደቡብ ሱዳን ለማረጋጋት የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት እና የአፍሪቃ ህብረት የሰላም እና የፀጥታ ጥበቃ ኮሚሽን በጋራ በመስራት ላይ መሆናቸውን አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/1JyZb
Südsudan Einwilligung Sationierung zusätzlicher Blauhelmsoldaten
ምስል picture-alliance/AP Photo/J. Lynch

[No title]

የደቡብ ሱዳናውያን ደህንነት ዋስትናን ለማረጋጋጥ እንዲያስችል ተጨማሪ 4,000 ሰላም አስከባሪዎች በዚያ እንዲሰማሩ የዓለሙ መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ አካል ያስተላለፈውን ውሳኔ የሀገሪቱ መሪዎች መጀመሪያ ላይ ከተቃወሙ በኋላ አሁን መቀበላቸው ተስፋ ሰጪ መሆኑ ተገልጾዋል። ደቡብ ሱዳን ውስጥ እጎአ ከ2011 ዓም ወዲህ 12,000 ሰላም አስከባሪዎች ተሰማርተዋል። የተጨማሪዎቹ ሰላም አስከባሪዎች ስምሪት ዝርዝር ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር በጋራ የሚዘጋጅ መሆኑን የተመድ እና አፍሪቃ ህብረት ባለስልጣናት አስታውቀዋል።


ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ


አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ