1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለጤና መረጃ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 30 2005

ስለጤና ጉዳይ የሚቀርቡ መረጃዎችን ምን ያህል ህዝብ እንደሚያገኛቸዉ፤ ወይም ለምን ያህል ህዝብ እንደሚደርሱ መገመት ይቸግራል። ነገር ግን አንድ ነገር ግልጽ ነዉ ሰዎች ለጤና ይዞታቸዉ ትኩረት መስጠትን ችላ ሊሉ አይገባም።

https://p.dw.com/p/19L5z
ምስል imago

 ጤና-ነክ ጉዳዮችን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ለማቅረብ መጣር የእኛን ኅብረተሰብ ሊነቃ ይችላል የሚል እምነት ያላቸዉ ወገኖች ራሱን የቻለ የጤና ድረገጽ ከፍተዉ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ወራት ተቆጥረዋል።

ዘመኑ የቴክኒዎሎጂ ነዉ የመረጃ፤ በአንዱ ጓዳ የተከሰተዉን ሌላዉ ባለበት ሆኖ ሊሰማዉ መንገዱ ተመቻችቷል፤ ለብዙሃኑ። በዘመነ ኢንቴርኔት ምስጢር የለም፤ ራዲዮና ቴሌቪዥን ዜናዎችን አልተከታተልኩም፤ የጤና ጉዳይ መረጃዎችን እንደልቤ አላገኝም ከሚባልበት ጊዜ ልንሻገርም ዳርዳር እያልን ይመስላል። አፍሪቃ ዉስጥም ቢሆን ይህ ዛሬ ብዙም የሚወራለት የራቀና ያልተደረሰበት ጉዳይ አይደለም።

Pressebild mysugr
ምስል mysugr.com/Ergun Kayis

ዛሬ ይላል የጤና አዳም ድረገጽ አንቀሳቃሽ፣ ዛሬ ሰዎች ለራዲዮና ቴሌቪዥኑ ጊዜ ቢያጡ እንኳ ከያሉበት በእጅ ስልካቸዉ በየመንገዱም ቢሆን የሚሹትን መረጃ ማንበብ ይችላሉ። የተለያዩ ወቅታዊ ዜናዎችን ከመዘገብ በተጓዳኝ ሄኖክ ዓለማየሁ ለጤና ጉዳይም ትልቅ ትኩረት መስጠቱን የሚያንቀሳቅሰዉ ድረ ገጽ ዘሃበሻ ይናገራል። ለጤና መረጃዎችን የምታጋራዉን ድረገጽም እዚያዉ ላይ ታዝላ ነዉ ያስተዋልኳት። አዘጋጅዋ  ለጤና ጉዳዮችን ትኩረት መስጠት ይገባል በሚል ለኢትዮጵያዉያን አንባቢዎቹ መረጃ በመስጠት ለማበረታታት ታስቦበት የተጀመረ መሆኑን ነዉ የሚናገዉ፤

ጋዜጠኛ ሄኖክ እንደሚለዉ ባላቸዉ መረጃ መሠረት በርካታ የድረገጹ ጎብኚዎች የሚገኙት እዚያዉ ሰሜን አሜሪካ ነዉ። ከኢትዮጵያስ ጎብኚዎች ይኖሩት ይሆን? ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ