1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግሥት መግለጫ

ዓርብ፣ ሐምሌ 8 2008

የኢትዮጵያ መንግሥት የክምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የፌደራል እና የክልል የፀጥታ ኃይላት ባደረጉት ርብርብ አካባቢው መረጋጋቱን ተናግረዋል ።

https://p.dw.com/p/1JPfa
Äthiopien Getachew Reda in Addis Abeba
ምስል DW/Y. Geberegeziabeher

[No title]


በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በጎንደር ከተማ የተከሰተው ግጭት መብረዱን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ ። የኢትዮጵያ መንግሥት የክምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የፌደራል እና የክልል የፀጥታ ኃይላት ባደረጉት ርብርብ አካባቢው መረጋጋቱን ተናግረዋል ። አቶ ጌታቸው በመግለጫቸው እንዳሉት በግጭቱ የሰው ሕይወት ጠፍቷል ንብረትም ወድሟል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ