1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስነ-ፅሁፎቻችን በአንዳንዶች ዐይን

ሐሙስ፣ የካቲት 6 2006

የአንድን ሀገር ወግ፤ ባህል፤ ታሪክ እና ሁለንተናዊ ጉዞን ለማወቅ፤ የህዝቦችዋን ባህላዊ የበዓል አከባበር፤ ስነ-ፅሁፎችዋን በተለይ ደግሞ ስነ- ግጥሞችዋን ተመልከት ሲሉ አንዳንድ ምሁራን ይገልፃሉ። በአሁኑ ወቅት በርካታ ገጣምያን በግጥም መድረኩ ሲሳተፉ ይታያል፤ በግጥም፤ እምቅ አድናቆትን በግጥም እምቅ ፍላጎትን፣

https://p.dw.com/p/1B88i
Afghanistan Kabul Buchhandlung Bücherei Bildung Kultur Buchladen
ምስል Hussain Sirat

በግጥም እምቅ ቅሬታን እየገለፁ በተለያዩ መድረኮች ጓደኝነት የፈጠሩ ጻህፍትም ጥቂት የሚባሉ አይደሉም። አንዳንድ ገጣምያን፤ ግጥምለአእምሮለልቦናናለስሜትየሚጥም፣ በስልትና በድንጋጌ የሚደረደር ቋንቋ ማለት ነው» ሲሉ ሌሎች ደግሞ ግጥም ኃይለ-ውበት(ዜማ) ፣ ኃይለ- ድቀት (ቅኔ)፣ ኃይለ-ቃል ሀያል ግጥም ነው። ይሉታል። አገላለፁ የማን እንደሆነ ባይታወቅም «ግጥም በጆሮ የሚደመጥ ስዕል ነዉ» መባሉንም በአንድ ድረ-ገጽ ላይ አንብቤአለሁ። በርካታ ወጣት ጻህፍት የስነ-ግጥም ክህሎታቸዉን የሚያሳዩበት፤ ግምገማ የሚቀበሉበት እንዲሁም እዉቀት የሚለዋወጡበት ድረ-ገጾችን ከፍተዉ ሲወያዩ ይታያል። ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ዘንድሮ በሳይኮሎጂ ትምህርት የሚመረቀዉ ወጣት ምስክር አክሊሉ በስነ ግጥሞቹ ይታወቃል፤ ግጥን መቋጠር የጀመረዉ ገና የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ሳለ እንደሆነ ነግሮናል። ወጣት አክሊሉ ግጥምን በቃላት የቆመ ንፁህ ነፍስ ያለው አካል ነው ይለዋል። በአሁኑ ወቅት እንደ ስነ ግጥም ሁሉ በርካታ ስነ-ፅሁፎችም በመጻህፍ መልክ እየታተሙ በገበያ ላይ መዋላቸዉ ይታያል፤ በአሁኑ ግዜ ገበያ ላይ አብዛኞቹ ስነ-ፅሁፎች ሰዎች በፖለቲካ ህይወታቸዉ የነበራቸዉን ተሞክሮ የሚያሳዩበት ነዉ በሚል ሂስ ሲሰነዘር ይሰማል፤ አዳዲስ መጻህፍትን በመገምገማቸዉ የሚታወቁትና በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ ሀገረሰባዊባህሎችማለት በፎክሎር ትምህርት የፒኤችዲ ተማሪ የሆኑት አቶ ገዛኸኝ ፀጋዉ እዉነት ነዉ ሲሉ፤ ኦስሎ ኖርዌ ነዋሪ የሆኑት አንጋፋዉ ጋዜጠኛ አበራ ለማ፤ በኛ ሀገር ስነ-ፅሁፉ ዓለም ከስነ- ግጥም ባሻገር በፖለቲካ ዙርያ ብቻ መጻህፍት በዙ በሚለዉ ሃሳብ እንብዛም አይስማሙም። በመጻህፍት ህትመት እና ስርጭት ስራ ላይ የተሰማሩት ደራሲ አስራት ከበደም ያላቸዉን አስተያየት ገልፀዉልናል። በስነ-ፅሁፍ ረገድ ያላቸዉን ያካፈሉንን የለቱን እንግዶቻችንን በዶቼ ቬሌ ስም እያመሰገንን፤ ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ መጫኛዉን በመንካት እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

Buchmesse Herat Afghanistan
ምስል DW/H.Hashimi

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ