ስዊድንና አዲሱ የድንበር ቁጥጥር
ማክሰኞ፣ ጥር 3 2008ማስታወቂያ
9.8 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ስዊድን በጎርጎሮሳዊው 2015፣ 163 ሺህ ተገን ጠያቂዎችን ነበር ወደ ሃገርዋ ያስገባችው ። ባለሥልጣናት እንደሚሉት ከዚህ ቀደም ሰዎች በነፃ በሚዘዋወሩበት ድንበር ላይ የጉዞ ሰነድ ቁጥጥር ተግባራዊ በተደረገበት በመጀመሪያው ሳምንት ሃገሪቱ 1500 የተገን ጥያቄ ማመልከቻዎችን ነው የተቀበለችው ። ባለፈው ጥቅምትና ህዳር ወር ውስጥ ግን ስዊድን በየሳምንቱ የምትቀበለው ወደ 10 ሺህ የሚጠጋ የተገን ጠያቂዎችን ማመልከቻ ነበር ። ስዊድን የድንበር ቁጥጥር ተግባራዊ ካደረገች ከአንድ ሳምንት በኋላ ሁኔታዎች ምን ይመስላሉ። ስዊድንና አዲሱ የድንበር ቁጥጥር በተመለከተ የስቶክሆልሙን ወኪላችንን አነጋግረነዋል።
ቴድሮስ ምህረቱን
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሃመድ