1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስደተኞችን ማገድ ያለዉሙት ትራምፕ

ሐሙስ፣ ጥር 18 2009

በዩናይትድ ስቴትስ የዶናልድ ትራምፕ በአዲስ ፕሬዝደንትነት መመረጥ ወደ ሀገሪቱ ለሚመጡ ስደተኞች መልካም ዜና አልሆነም። ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸዉ ወቅት ስደተኞችን እንደማይቀበሉ እና በሕገወጥ የገቡትንም አባርራለሁ በማለት ዝተዉ ነበር።

https://p.dw.com/p/2WSo9
USA Trump unterzeichnet das Dekret zum Grenzzaun mit Mexiko
ምስል Getty Images/AFP/N. Kamm

mmt Beri. Washington DC (Trump and Refugee) - MP3-Stereo

በትናንታናዉ ዕለት ታዲያ ሕገወጥ ተሰዳጆች ይገቡበታል ያሉትን ከሜክሲኮ ጋር ሀገራቸዉን የሚያዋስነዉን የድንበር አካባቢ በግንብ ለማጠር ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ዉሳኔያቸዉ ያስቆጣት ጎረቤት ሜክሲኮም እንደሚሉት የግንቡን ወጪ አልከፍልም ብላለች። ትራምፕ በዚህ አላበቁም ለሽብር ስጋት ካሏቸዉ ኢራቅ፣ ሶርያ፣ ኢራን፣ ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ እና የመን ለ30 ቀናት የይለፍ ወይም ቪዛ ፈቃድ ጥያቄ እንዲያዝ የሚያደርግ መመሪያም እያወጡ ነዉ። አዲሱ የአሜሪካን ፕሬዝደንት የፎከሩትን ተግባራዊ ከማድረጋቸዉ አስቀድሞ ለጥቂት ወደ አሜሪካ የገቡ ተሰዳጆች መኖራቸዉን የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ