1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስደተኞች፤ አዉሮጳና አፍሪቃ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 15 2007

የሕብረቱ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ዕቅዱ ተመሳሳይ እልቂት እንዳይደገም ለመከላከልና ስደተኞችን ለመርዳት የሚጠቅም ነዉ።አዉሮጳን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ድላሚኒ ዙማ ከአዉሮጳ አቻዎቻቸዉ ጋር ያደረጉት ዉይይት ያተኮረዉም በስደተኞች ይዞታና በስደት ምክንያቶች ላይ ነበር።

https://p.dw.com/p/1FDiI
ምስል picture-alliance/dpa/ Y.Valat

ከሊቢያ ወደ አዉሮጳ ይጓዙ የነበሩ ከስምንት መቶ በላይ ስደተኞች ባለፈዉ ቅዳሜ ማታ ሜድትራኒያን ባሕር ላይ ሰጥመዉ ማለቃቸዉ የፈጠረዉ ድንጋጤ የተለያዩ ወገኖችን ለመፍትሔ እያባተለነ ነዉ።የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት መሪዎች ከዚሕ ቀደም ሚንስትሮቻቸዉ ያረቀቁትን ባለ አስር ነጥብ ዕቅድ ለማፅደቅ ዛሬ ብራስልስ-ቤልጅግ ዉስጥ ላስቸኳይ ጉባኤ ተቀምጠዋል።የሕብረቱ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ዕቅዱ ተመሳሳይ እልቂት እንዳይደገም ለመከላከልና ስደተኞችን ለመርዳት የሚጠቅም ነዉ።አዉሮጳን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ድላሚኒ ዙማ ከአዉሮጳ አቻዎቻቸዉ ጋር ያደረጉት ዉይይት ያተኮረዉም በስደተኞች ይዞታና በስደት ምክንያቶች ላይ ነበር።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ