1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስድስተኛዉ ፓትሪያርክ ተመረጡ

ሐሙስ፣ የካቲት 21 2005

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስድስተኛ ፓትሪያርክ ምርጫ ዛሬ ተካሂዷል። በቤተክርስቲያኒቱ የስብሰባ አዳራሽ ሙሉ ቀን በተካሄደ የምርጫ ስርዓትም በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ተመርጠዋል።

https://p.dw.com/p/17o4P
ምስል DW

ለምርጫዉ በእጩነት አምስት ሊቃነጳጳሳት የቀረቡ ሲሆን ከተሰጠዉ ስምንት መቶ ስድስት ድምፅ አምስት መቶዉን ማግኘታቸዉን የአስመራጭ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ ገልፀዋል።  የ 71 ዓመቱ ሊቀ ጳጳስ በዓለ ሢመታቸው የፊታችን እሁድ በመንበረ ጸባዖት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚከናወን ተነግሮአል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ