1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስጋት ያጠላበት የየመን የፀጥታ ይዞታ

ሐሙስ፣ መስከረም 29 2007

በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ በዛሬዉ ዕለት በደረሰ አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ፍንዳታ ከ40 በላይ ሰዎች ህይወት መጥፋቱንና ከ70 በላይም መጎዳታቸዉን የሀገሪቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የጠቀሱ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

https://p.dw.com/p/1DSma
Jemen Kämpfe Sanaa 20.09.2014
ምስል Reuters/Khaled Abdullah

በያዝነዉ ሳምንት በመዲና ሰንዓ ተመሳሳይ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ሲደርስ የዛሬዉ ሁለተኛ መሆኑ ነዉ። ጥቃቱ ፣ የሁቲ ዓማፅያን ቡድን ያካሄዱትን ተቃውሞ ዒላማ ያደረገ ነበር።ከዚህም ሌላ በሀገሪቱ ደቡብ ምስራቅ ክፍለ ሃገር በሚገኝ ሃዳርሙት በተባለ ስፍራም በአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት 19 የመንግስት ወታደሮች መገደላቸዉ ተዘግቧል። የመን ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2011,ም አንስቶ ከገባችበት የፖለቲካ ዉዝግብ ወጥታ የተጠናከረ መንግስት መመስረት እንደተሳናት እየታየ ነዉ። በዚህ ሳምንት የሀገሪቱ ፕሬዝደት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሰየሟቸዉ ፖለቲከኛም ተቀባይነት እና እውቅና ያላገኙት የፕሬዚደንታዊው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አህመድ አዋድ ቢን ሙባረክ ጥቃቶቹ ከመጣላቸው ከጥቂት ሰዓታት በፊት ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል። የየመንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክታ ሸዋዬ ለገሠ ሰንዓ የሚገኘዉን ተባባሪ ዘጋቢ ግሩም ተክለሃይማኖትን በስልክ አነጋግራዋለች። ግሩም የደረሰዉን የቦምብ ጥቃትና የጸጥታዉን ሁኔታ አስመልክቶ በማብራራት ይጀምራል።

ግሩም ተ/ሃይማኖት

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ