1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስፖርት 23 08 2009

ሰኞ፣ ሚያዝያ 23 2009

አትሌቲክስ በጀርመን ዲሺስልዶርፍ የወጣቶች ማራቶን ውድድር ዩጋንዳዊው ሮበርት ችሞንግ ሲያሸንፍ ፤ በቱርክ ኢስታንቡል ትላንት በተደረገው የግማሽ ማራቶን  ውድድር ደግሞ የ23 ዓመትዋ ኬንያዊት ሩት ቺፕናጊች እና የታንዛኒያው ኤስማል ጁማ ድል ቀንቷቸዋል።

https://p.dw.com/p/2cBsN
Tennis WTA Stuttgart Frauen Finale Laura Siegemund - KiKi Mladenovic
ምስል picture-alliance/dpa/B. Weißbrod

ስፖርት 23 08 2009

እግር ኳስ

ሊጠናቀቅ 4 ጨዋታዎች በሚቀሩት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫው እንደተበላ ዕቁብ ተቆጥሮ አራቱ በእግር ኳስ የጠነከሩ ኃያላን ቡድኖች ሊቨርፑል፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና የሰሜን ሎንደኑ አርሰናል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስተኛ እና አራተኛ ሆኖ ለመጨረስ ምጥ ላይ ናቸዉ። 

ቦክስ

በብሪታንያ የቦክስ ስፖርት ታሪክ  90 ሺህ  ተመልካች  እና 140 ሃገራት ዘጋቢዎች በተከታተሉት የቦክስ  ውድድር አንቶኒ ጆሽዋ ቭላድሚር ክሊችኮን በመዘረር አሽናፊ ሆንዋል።  

የሜዳ ቲንስ

በስፔን ሲካሂድ በቆየው የባርሲሎና ኦፕን የሜዳ ቴኒስ ውድድር ራፋኤል ናዳል ሽቱትጋርት ስቲትጋርት በተካሂደው የሲቶች ግራንድ ፕሪክስ  ውድድር የጀርመንዋ ሎራ ሴጅመንድ አሽናፊ ሆኑ። ሙሉ ቅንብሩን ከድምጽ ገዘባዉ ያድምጡ።

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ