1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማሊያና ተመድ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 13 2009

ድርጅቱ እንደሚለዉ ሶማሊያ ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እና ከአካባቢዉ ማሕበራት ጋር የመሠረችዉ ትብብር የፀጥታ ኃይሏን ለማጠናከር፤ ረሐብን ለመከላከል፤ ሙስናን ለመዋጋት እና የመንግሥቱን መዋቅር ለማጎልበት ጠቃሚ ነዉ

https://p.dw.com/p/2bhT6
Somalia Mogadischu - U.N. Generalsekretär Antonio Guterres bei Pressekonferenz
ምስል Reuters/F. Omar

M M T/ (Beri.WDC) Somalia-UNO - MP3-Stereo

የሶማሊያ መንግሥት የሐገሪቱን ፀጥታ ለማስከበር እና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ተባብሮ እየሠራ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።ድርጅቱ እንደሚለዉ ሶማሊያ ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እና ከአካባቢዉ ማሕበራት ጋር የመሠረችዉ ትብብር የፀጥታ ኃይሏን ለማጠናከር፤ ረሐብን ለመከላከል፤ ሙስናን ለመዋጋት እና የመንግሥቱን መዋቅር ለማጎልበት ጠቃሚ ነዉ።የሶማሊያን ጉዳይ የሚከታተሉ አንድ የማሕበራዊ ጉዳይ ምሑር ግን የዓለም አቀፉን ድርጅት ተስፋ ብዙም አልተቀበሉትም።የዋሽንግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ