1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጦር መውጣት በኋላ

ሰኞ፣ ጥር 18 2001

የመጨረሻዎቹ የኢትዮጵያ ወታደሮች ዛሬ ጠዋት ወጥተዋል። ከሶማሊያ ሙሉ በሙሉ ወጥተዋል። በባይዶዋ ብቻ ነበር የቀሩት፤ እነሱም ትናንት ማታ ለቀዋል። አሁን ባዶ በቀሩት ወታደራዊ ይዞታዎች ግጭት ተፈጥሮ ፖሊስና ታጣቂ ሚሊሺያን ጨምሮ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል።

https://p.dw.com/p/GgaV
ሶማሊያ
ሶማሊያ
የኢትዮጵያ ጦር ዛሬ ጠዋት ሶማሊያን ሙሉ በሙሉ ለቆ መውጣቱ ተገለፀ። በተፈጠረው የሀይል ክፍተት የሶማሊያ የሽግግር መንግስት ስጋት ውስጥ ወድቓልም ተብሏል። በዚህ ሳምንት ጅቡቲ ውስጥ ሊደረግ በታቀደው ሁሉን አቀፍ የሶማሊያውያን ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ የሶማሊያ ህግ አውጪ አካላት ደግሞ አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀዋል።