1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶሪያ፤ ውጊያውና የ ተ መ ድ፣

ዓርብ፣ ነሐሴ 11 2004

የሶሪያ ጦር ሠራዊትና አማጽያን በዛሬው ዕለት፤ በመዲናይቱ በደማስቆ፣ወታደራዊው አኤሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ አካባቢ መጋጨታቸው ተነገረ። ደቡባዊውን የመዲናይቱን ከፊል ፣ ጦር ሠራዊቱ በመድፍ መደብደቡን የሶሪያ የሰብአዊ መብት ይዞታ ታዛቢ ቡድን

https://p.dw.com/p/15s89
ምስል Reuters

ጠቁሞአል። በደቡባዊው የደማስቆ መዳረሻ፤ ሌሊቱን ያተተቋረጠ ውጊያ የተካሄደ ሲሆን ፤ በዚያም አማጽያኑ ተጠናክረው መገኘታቸው ነው የተገለጠው። በሰሜናይቱ የወደብ ከተማ ፤ አሌፖ፤ በአማጽያኑ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ የከተማይቱ ክፍሎች በከባድ መሣሪያ ተደብድበዋል። የሶሪያው ውጊያም ሆነ ቀውስ ጎረቤት ሊባኖስን ማወኩ አልቀረም።

Ban Ki-Moon UN Sicherheitsrat Syrien
ምስል AP

የሶሪያው ውዝግብ በጦር ሠራዊቱና በአማጽያኑ አጸፋዊ እርምጃ ጭካኔ እየታየበት ስለመሆኑ የተባበሩት መንግሥታት፤ የሰብአዊ መብት ም/ቤት አጥኚ ቡድን ማስገንዘቡ የሚታባል አይደለም። የተባበሩት መንግሥታት ከነገ በስቲያ እሁድ ድረስ ጸንቶ የሚቆየውን የታዛቢዎችን በዚያ የመቆያ ጊዜ ፤ የጊዜ ገደብ እንደማያራዝም አስታውቋል። አዲሱ፤ ልዑክ ፤ አልጀሪያዊው ዲፕሎማት ፣ ላኽዳር ብራሂሚ የሚበጅ ነገር ለማከናወን እጅግ ከባድ ሁኔታ ማጋጠሙን ሳይገልጹ አላለፉም። ታዛቢው ቡድን ፣ በሶሪያ ቢቆይ በተባበሩት መንግስታት የሩሲያ አምባሰደር ቪታሊ ቹርኪን ፤ አብዛኞቹን የፀጥታ ጥበቃው ም/ቤት አባላትን፤ በሶሪያ የኅይል እርምጃ ተግትቶ ፣ የፖለቲካ መፍትኄ እንዲገኝ ያሳዩት ጥረት ልባዊ አይደለም በማለት መንቃፋቸው ነው የተመለከተው።

Syrische Flüchtlinge im Libanon
ምስል Don Duncan

«እነዚህ አገሮች፣ የኅይል እርምጃው ቆሞ፤ ለሶሪያ የፖለቲካ መፍትኄ እንዲገኝ እውነተኛ ጥረት አይደለም ያሳዩት።»

በሶሪያ የተባበሩት መንግሥታት ታዛቢ ቡድን አባላት የተሰጣቸውን ኀላፊነት በአወንታዊ መልኩ ፍጻሜ ላይ ለማድረስ ሳይቻላቸው መቅረቱ የሚታወስ ነው። እንዲያውም ባለፈው ሰኔ አጋማሽ ገደማ አብዛኛውን ጊዜ ካረፉበት ሆቴል ሳይወጡ ፤ ሳይንቀሳቀሱ ነበረ ፣ ጊዜያቸውን ያሰለፉት። ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ግን፤ ታዛቢው ቡድን ቢወጣም፤ ድርጅታቸው ከሶሪያ ጋር ግንኙነቱን ማቋረጥ እንደሌለበት ነው ያስገነዘቡት። በዚህ ረገድ ያቀረቡት ሐሳብም በድምጽ መደገፉ አልቀረም። በተባበሩት መንግሥታት የፈረንሳይ አምባሳደርና የወቅቲቱ የፀጥታ ጥበቃው ም/ቤት ፕሬዚዳንት ጀራ አሮ--

«በደማስቆ አንድ አገናኝ ጽ/ቤት እንዲከፈት የቀረበውን ሐሳብ በድምፅ ደግፈነዋል።»

Syrische Kurden
ምስል AP

በሶሪያ ከ 20 እስከ 30 ሠራተኞች የሚገኙበት አዲስ የተባበሩት መንግሥታት የውክልና ጽ/ቤት እንዲከፈት መባሉን ጀርመን ደግፋለች። ይሁንና፤በተባበሩት መንግሥታት፤ የበርሊን መንግሥት ተወካይ ሚጌል በርገር እንዳሉት፤ አገናኝ ቢሮው፤ በቂና ችሎታ ያላቸው ሠራተኞችን ማሠማራት ይኖርበታል ።

«ይህን አጥብቀን እንደግፋለን። ምክንያቱም የፖለቲካ ግንኙነቱ፣ ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ሥራና ፤ ለሰብአዊ እርዳታ ይበጃልና ነው። ስለዚህ በዚያ የተባበሩት መንግሥታት መገኘትም ሆነ መወከል፣ ባስቸኳይ ተፈላጊ ነው።»

የሶሪያውን ውጊያ ገትቶ የፖለቲካ መፍትኄ እንዲገኝ ሐሳቡ ቢኖርም፤ ውዝግቡ ሶሪያን አልፎ ጎረቤቲቱን ሊባኖስን እያመሰ ነው። ሶሪያ ውስጥ፣ 11 ሊባኖሳውያን ተሳላሚዎች ባለፈው ግንቦት ተጠልፈው ከተወሰዱ በኋላ፤ ከትናንት በስቲያ ፣ አዛዝ በተባለችው ሰሜናዊ ከተማ መንግሥት በወሰደው በአየር የማጥቃት ዘመቻ ተገድለዋል የሚል ወሬ በመናፈሱ፣ከ 20 በላይ ሶሪያውያን ወደ ቤሪሩት አኤሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ሲያመሩ ታፍነው መወሰዳቸውና ሱቆቻቸውም መመዝበራቸው ተነግሯል።

የሶሪያውን ፕሬዚዳንት በሺር ኧል አሰድን መንግሥት የምትቃወመው ስዑዲ ዐረቢያ ፤ ዜጎቿ ዛቻ እየተሰነዘረባቸው በመሆኑ ፤ ከሊባኖስ ባስቸኳይ እንዲወጡ ማዘዝ ግድ ሆኖባታል። የዐረብ አሚሮች ኅብረትና ቓታርም ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል። በአሁኑ ሞቃት ወቅት፤ የባህር ሰላጤው አካባቢ አገሮች ዜጎች፤ ከሐሩሩ አካባቢአቸው፤ ትንሽ ቀዝቀዝ ያለ የሜድትራንያን አየር ጠባይና ፈታ ያለ ማኅበራዊ ኑሮም ወደሚንፀባረቅባት ሊቢኖስ በየጊዜው በ«ቱሪስትነት» ይጎርፉ እንደነበረ የታወቀ ነው።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ