1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶሪያ የግጭት-እልቂት ምድር

ሰኞ፣ ሰኔ 4 2004

የሶሪያ ሕዝብ በፊት የበሽር አል-አሰድን አገዝ ለመቃወም ያበረዉ ከተጫነበት ጭቆና ለመላቀቅ በጣሙን እንደግብፅና እንደ ቱኒዚያ ብጤዎቹ የተሻለ አስተዳደር፥ ዲሞክራሲ ብልፅግናን በመመኘት ነበር።ተስፋ ምኞቱ በእልቂት ፍጅት መቀጨቱ እንጂ-የዛሬዉ ቁጭት።

https://p.dw.com/p/15CGo
Students lay on the ground to depict a massacre as they take part in an anti-government protest at Aleppo University, June 4, 2012. Picture taken June 4, 2012. REUTER/Handout (SYRIA - Tags: CIVIL UNREST POLITICS) FOR EDITORIAL USE ONLY. NOT FOR SALE FOR MARKETING OR ADVERTISING CAMPAIGNS. THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS
ሙታንምስል Reuters



የመካ-መዲና ምዕመናን ለሶሪያ ሠላም ዱዓ-ስግደቱን ሲያንቆረቁሩት፣ የሪያድ፣ የዶሐ፣ የአንካራ ፖለቲከኞች የደማስቆ ገዢዎችን የማስጠፋት አላማ-እቅዳቸዉን ያዥጎደጉዱታል።ዋሽንግተን፣ ለንደን፣ ፓሪሶች የደማስቆ ገዢዎችን የመቅጣት ዛቻ-ማስጠነቂያ በናረ ቁጥር፣የሞስኮ ቤጂንጎች ተቃዉሞ ይግማል።የኮፊ አናን ሠላም የማስፈን ዲፕሎማሲ ከበጎ ተስፋ አፋፍ ላይ መድረሱ ሲነገር፣ጄኔራል መሕር አል-አሠድ ከደማስቆ፣ ኮሎኔል ሪያድ አል-አሰድ ከሐታያ (ቱርክ) የሚያዟቸዉ ወታደሮች በጋራ ሐገራቸዉ ላይ ቦብ-ጥይት እየዘሩ፣ የሚያጭዱት አስከሬን ይከመራል።ሶሪያ-ለምን ደግሞስ እስከ መቼ? ላፍታ አብረን እንጠይቅ።
            
ሐሙስ፥-ኒዮርክ።«ሚስተር ፕሬዝዳንት እዚያጋ ላፍታ ቆም ልበልና ትናንት ከሐማ በስተምዕራብ አል-ኮፉር ዉስጥ ልጆችና ሴቶችን ጨምሮ በአስር የሚቆጠሩ ሠላማዊ ሰዎች በመገደላቸዉ የተሰማኝን ድንጋጤ እና ዉግዘቴን እንድገልጥ ይፈቀድልኝ።ለሰለቦቹና ለቤተሰቦቻቸዉ ሐዘኔን እገልጣለሁ።የሰዎች ግድያ የሶሪያ የዕለት ከዕለት እዉነታ እንዲሆን መፍቀድ አንችልም።»

በሶሪያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ ኮፊ አናን።አናን ያወግዛሉ፥ ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን «እስከ መቼ?» ይላሉ።
              
«ሥንቴ ነዉ የምናወግዘዉ።ንዴታችንን የምንገልፅበት መንገድስ ሥንት ነዉ።»

ሶሪያ ግን ትነዳለች።ትደማለች።ታነባለችም።የአስከሬን፥ የደም-እምባ ምድር።አርብ እንደ ሐይማኖት-ባሕሉ ወግ ለሙስሊሙ የጋራ-ሥግደት፥ የትልቅ ፀሎት ክቡር ዕለት ነዉ።ለቀቢራ ነዋሪዎች ግን-የአናን ዉግዘት፥ የፓን ጥያቄ ከኒዮርክ በተሰማ ማግስት የነበረዉ አርብ የወገኖቻቸዉን አስከሬን የቆጠጥሩ፥ የቀብሩበት፥ደም አጥንታቸዉን ያፀዱ የለቀሙበት፥ ያለቀሱ-ያነቡበት ቀን።
             
«ልጆች፥ ሕፃናት፥ ወንድሜ፥ ሚስቱ እና ሰባት ልጆቻቸዉ ሁሉም አለቁ።ትልቁ ልጃቸዉ ገና የስድስተኛ ክፍል ተማሪ ነበር።ቤቱን እንዳለ ነዉ-እንዳለ ያጋዩት።»

በዚያ አርብ፥ በዚያች መንደር ብቻ ሰባ-ስምንት ሠላማዊ ሰዉ ተገደለ።ቁጥሩ ይበልጥም-ያንስም ይሆናል።የገዳዮቹ ማንነት ግን እንደየባለጉዳዩ አቋም ተቃራኒ ወይም እንደየተመልካቹ ፍላጎት የተለያየ ነዉ።መንግሥት «አሸባሪ ታጣቂዎች» የሚላቸዉን ተቃዋሚዎቹን ይወነጅላል።ተቃዋሚዎቹና ደጋፊዎቻቸዉ ደግሞ የመንግሥት ጦርን።

ገቢራዊነቱ ያልሠመረዉን የሠላም ዉል ለመከታተል የዘመተዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የታዛቢዎች ቡድን ባንድ ነገር እርግጠኛ ነዉ።ሰላማዊ ሰዎች በመገላቸዉ።
             
«በመንደሪቱ የተቃጠለ አስከሬን ሽታ-ይቀረናል።የሟቾች አካል በየሥፍራዉ ተበታትኗል።»
የታዛቢዉ ቡድን ቃል አቀባይ ሳዉሳን ጎሼን።
                   
ባለፈዉ አንድ ዓመት ከመንፈቅ፥ ሆምስ፥ ዳራ፥ ደማስቆ፥ አል ኩቢር እና ሌሎችም ከተሞችና መንደሮች አስር ሺዎችን እንደ ገደሉ፥ እንዳቆሰሉ እንዳፈናቀሉት ሐይላት ሁሉ የቀቢራን ነዋሪዎች የገደሉ-ያስገደሉት ወገኖች ማንነትም ግልፅ አይደለም።ቃል አቀባይ ጎሼንም ቡድናቸዉ የደረሰዉን መረጃ «የተሳከረ» ከማለት ባለፍ የገዳዮችንም ሆነ የሟቾችን ማንነት አያዉቁም።
               
«መረጃዎቹ እርስ በርስ የሚቃረኑ ናቸዉ።ማጣራት አለብን።የሟቾቹንና የጠፉትን ሰዎች ስም ማመሳከር አለብን።»

በጋዜጣዉ መግለጫዉ፥ ሐዘን ዉግዘቱ፥ በሠላም-ዉል፥ ሥምምነቱ መሐል የሶሪያዎች ግጭት፥ ግድያ እልቂቱ ቀጥሏል።የዘመኑ ዓለም፥- ዲፕሎማት-ፖለቲከኛ፥ምሁር-ባለሙያ በየስፍራዉ፥ በየጊዜዉ ለሚከሰቱ ግጭት-ግድያዎች ፍትሔ እንደሚለዉ ሁሉ ሶሪያን ለሚያብጠዉ ቀዉስም አብነቱ የሶሪያዎች መስማማት ነዉ ባይ ነዉ።

ለሶሪያ መንግሥት ታዳላለች የምትባለዉ የቻይና ምክትል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ቼንግ ጉኦፒንግ ባለፈዉ ሳምንት ይሕንን ቃል ደገሙት።
              
«የዉጪ ሐይላት በየትኛዉም መንገድ በሶሪያ የዉስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸዉን አጥብቀን እንቃወማለን።የሶሪያ ዉዝግብ በሶሪያ ሕዝብ በራሱ መፍትሔ ማግኘት አለበት።»

ሐሳቡ ለሶሪያ ብቻ ሳይሆን ዉዝግብ ላለበት ለየትኛዉም ሐገር በርግጥ ድንቅ ነዉ።የዓለም ሐያላን ጣልቃ-ያልገቡበት የዓለም ታሪክ አለመኖሩ፥ ሶሪያዎች ከየዘመኑ ሐያላን ጣልቃ ገብነት የፀዳ ታሪክ የሌላቸዉ የመሆኑ ሐቅ-እንጂ ሕቅታዉ።

እርግጥ ነዉ ከ222 እስከ 238 ዓመተ ዓለም ዓለምን ያስገበረዉ የሮማ ቄሳር አሌክሳንደር ሴቨረስ ሶሪያዊ ነበር። ከሁለት መቶ አስራ-ስምንት እስከ ሁለት መቶ ሃያ-ሁለት ዓመተ-አለም የሮማ ሥርወ-መንግሥትን የዘወረዉ የሴቬረስ ያጎት ወይም ያክስት  ያክስት ልጅ ንጉስ ኤላጋባሉስም ሶሪያዊ ነበር።ከሁለት መቶ አርባ-አራት እስከ ሁለት መቶ አርባ ዘጠኝ ዓመተ-ዓለም ዓለምን የገዛዉ የሮማዉ ንጉስ ፊልሊፕ የአረቡ ወይም ማርቆስ ጁሉየስ ሶሪያዊ ነበር።

ከኻሊድ ኢብን አል-ወሊድ እስከ አብዱል አል መሊክ፥ እስከ አል ወሊድ ቀዳማዊ የተፈራረቁት የመምሉክ ኸሊፋቶች ደማስቆ ተቀምጠዉ እስከ ስጳኝ የሚደርስዉን ዓለም በየተራ ገዝተዋል።ሶሪያ ግን ሐያላን ይፈራረቁባት እንጂ ለሕዝቧ የጠቀመ በሕዝቧ ፍቃድ የነገሠ-በሕዝቧ ድምፅ የተመረጠ መሪ ጥንትም፥ ድሮም አልነበራትም።ዛሬም የላትም።
                

የጥንቶቹ ፋርሶች የቅርብ ጎረቤቶቻቸዉ ከክርስቶስ ልደት በፊት 10 ሺሕ ዓመት ጀምሮ የገነቡትን ባሕል፥ የደረሱበትን እዉቀት ሥልጣኔ ለማየት ወደ ምሥራቅ፣ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብ እንዳማተሩ ዘመነ-ዘመናት መጠበቅ ነበረባቸዉ።በሰባተኛዉ ዓመተ-ዓለም ግድም ወደ ምዕራብ ሲቃኙ ግን የዳበረዉን የኒዮሌቲክ ባሕል ተመለከቱ።ሰዉ መሬት አርሶ፣ ከብት አርብቶ የማምረት፣ የመብላት ጥበብን ከሶሪያዎች ተማሩ።የሶሪያዎችን ጥበብ ሥልጣኔ-ከሶሪያዎች በላይ የተራቀቁበት ፋርሶች ሴይሩስ በተባለ ጀግናቸዉ መሪነት በዓምስት መቶ ሐምሳ ዓመተ ዓለም ግድም አስልጣኝ-አስተማሪዎቻቸዉን አስገበሩ።

የሆሜር ትረካ፣ የፕሌቶ ጥያቄ በየየነበሩበት ዘመን የነበረዉ የግሪክ ማሕበረሰብ እድገት ነፀብራቅነቱ፥ የየግል ብስለታቸዉ ዉጤትነቱ አያነጋግረግርም።የግሪኮቹ እድገት፣ የትልቅ አሳቢዎቻቸዉ ብስለት መሠረቱ ግን ከሜድትራኒያን በስተደቡብ በሚገኘዉ በእዚያ ምድር የተፀነሰዉ ሥልጣኔ መሆኑ በርግጥ አያጠያይቅም።

አሪስቶትል እንደ ብዙ ደቀመዛሙርቱ ሁሉ የሜቂዶንያዉን አልጋ ወራሽ ያሳደገዉ ከቀዳሚዎቹ የቀሰመዉን፣ ሶሪያ ላይ የደባረዉን፣ እራሱ የቀመረዉን ጥበብ እያስተማረ ነበር።አስራ-ስድስት አመት እስኪሞላዉ ድረስ የአርስቶትልን እዉቀት እየመገመገ ያደገዉ ያ ወጣት የአባቱን አልጋ ወርሶ ግዛቱን ለማስፋፋት «አንድ» ያለዉ የልጅነት ዕዉቀቱ መሠረት ወደሆነዉ አካባቢ ነበር።ኋላ «ታላቁ» ከሚል ቅፅል ጋር የሚታወቀዉ የሜቅዶኒያዉ ወይም የግሪኩ ንጉስ አሌክሳንደር ሳልሳዊ የፋርሶቹን ሥርወ መንግሥት ደምስሶ የዛሬዋን ሶሪያንና መላዉን የፋርስ ግማደ ግዛትን አስገበረ።


ግብፆች አሰሪያዎችን፥ ግሪኮች፥ ፋርሶችን፥ አርመኖች፣ግሪኮችን፥ ሮሞች፣ አርመኖችን፥ዑመያዶች፣ ሮሞችን፥ አብሲያዶች፥ ዑመያዶችን፥ ቱርኮች፥ የመስቀል ጦረኞችን  እያስገበሩ፥ ለየተተኪዎቻቸዉ እየገበሩ ሲወድቁ የእርሻ ጥበብ፥ የከብት እርባታ ብልሐት የፈለቀበት፥ ፊደል-ሐይማኖት የዳበረባት ምድር ሕዝብ ለየባለዘመኑ ከመገዛት ወይም የሚፈራረቁ ገዢዎችን ከመመልከት ባለፍ ሥለ ራሱ የመወሰን አቅም፣ እድል፥አጋጣሚም አልነረዉም።ዛሬም እንዲያ ነዉ።

የመጨረሻዎቹ የሶሪያ ቅኝ ቀዢዎች ፈረንሳዮች ደማስቆን ሙሉ በሙሉ ለቀዉ የወጡት በ1941 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ነበር።ከያኔ በሕዋላም በእስከ ዛሬዋ ሶሪያ አይደለም-በወደፊቷ  ጉዞ እንዴትነት ዛሬም የሚሻኮቱት ግን ከሶሪያዎች በላይ የዋሽግተን-ለንደን፥ የቤጂግ-ሞስኮ ሐያላን፥ አለያም የቴሕራን-ሪያድ፥ የአንካራ-ዶሐ ተከታዮቻቸዉ ናቸዉ።
                      
«ትናንት ሐማ ዉስጥ ያየነዉ በሥርዓቱ ድጋፍ የተፈፀመዉ አመፅ ፈፅሞ ተቀባይነት የለዉም።አሳድ ጭካኔያቸዉን በእጥፍ ጨምረዋል።እና አሳድ እስካልተወገዱ ድረስ ሶሪያ ሰላማዊ፥ የተረጋጋች ወይም ዴሞክራሲያዊ አትሆንም፥ ልትሆንም አትችልምም።»

ወይዘሮ ሒላሪ ክሊንተን።የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር።የሶሪያ ሕዝብ የራሱን ችግር እራሱ ማስወገድ አለበት።ግን ደግሞ የሶሪያዉ መሪ መወገድ አለባቸዉ።ጣልቃ-መግባት አለመግባት፥ አንድና---ብዙ።


የ1941ዱ ነፃነት ለሶሪያ ሕዝብ ከዉጪ አገዛዝ የመላቀቁ ማረጋገጪያ የሰላም-ብልፅግናዉ ብልጭታ፥ በራሱ ወገኖች የመተዳደሩ ጅምር መስሎ ነበር።ከሐሺም አል-አታሲ እስከ አብድ አል ከሪሚ፥ ከአሚን ሐፊዝ፥ እስከ ሐፊዝ አል-አሰድ የተፈራረቁት ፖለቲከኞችና የጦር ጄኔራሎች የጥንታዊቱን ሐገር ሥልጡን ሕዝብ እንደ ዉጪዎቹ ገዢዎች ረግጠዉ ገዙትን እንጂ የተከሩት የለም።


የሶሪያ ሕዝብ ከዓመት ከመንፈቅ በፊት የበሽር አል-አሰድን አገዝ ለመቃወም ያበረዉ ከዉጪ አገዛዝ ከተላቀቀ ወዲሕ ከተጫነበት ጭቆና ለመላቀቅ በጣሙን እንደግብፅና እንደ ቱኒዚያ ብጤዎቹ የተሻለ አስተዳደር፥ ዲሞክራሲ ብልፅግናን በመመኘት ነበር።ተስፋ ምኞቱ በእልቂት ፍጅት መቀጨቱ እንጂ-የዛሬዉ ቁጭት።
                

ወይዘሮ ክሊንተን ለሶሪያ ሰላም አሰድ መወገድ አለባቸዉ ሲሉ፥ የሩሲያዉ አቻቸዉ ሰርጌይ ላቫሮቭ ደግሞ ለሶሪያ ሠላም አዲስ ጉባኤ ይጠራ ይላሉ።ሁሉም ግን አንድ ነገር በማለት አንድ ናቸዉ።በሶሪያ ጉዳይ ጠልቃ-አንገባም።ዓለም ሁሉ ደግሞ ባንድ ነገር አንድ ነዉ። እስካሁን ማንም ሶሪያ ከድቀት፥ ሕዝቧን ከዕልቂት ባለማዳኑ።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።
 

Source News Feed: EMEA Picture Service ,Germany Picture Service Lebanese army soldiers take position in their armoured vehicle as gunmen are seen in the background at the Sunni Muslim Bab al-Tebbaneh neighbourhood in Tripoli, northern Lebanon, during clashes May 16, 2012. Heavy fighting rocked Lebanon's northern port of Tripoli for a fourth day on Wednesday, wounding at least six people in a city where sectarian tensions have been growing over the revolt in neighbouring Syria, security sources said. REUTERS/Omar Ibrahim (LEBANON - Tags: POLITICS CIVIL UNREST MILITARY)
ገዳዩምስል Reuters
Demonstrators protest against Syria's President Bashar Al-Assad in Kafranbel, near Idlib April 24, 2012. The banner reads, "Occupied Kafranbel". Picture taken April 24, 2012. REUTERS/Raad Al Fares/Shaam News Network/Handout (SYRIA - Tags: POLITICS CIVIL UNREST) FOR EDITORIAL USE ONLY. NOT FOR SALE FOR MARKETING OR ADVERTISING CAMPAIGNS. THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS
Syrien Homs Demonstrationምስል Reuters
Demonstrators protest against Syria's President Bashar Al-Assad in Kafranbel, near Idlib, April 25, 2012. REUTERS/Raad Al Fares/Shaam News Network/Handout (SYRIA - Tags: CIVIL UNREST POLITICS CONFLICT) FOR EDITORIAL USE ONLY. NOT FOR SALE FOR MARKETING OR ADVERTISING CAMPAIGNS. THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS
የሕፃናት ሰልፍምስል Reuters
A man rests in his temporary home after fleeing Taldou, near Houla, following last week's massacre, June 5, 2012. Picture taken June 5, 2012. REUTERS/Saria Al Holany/Handout (SYRIA - Tags: CIVIL UNREST POLITICS) FOR EDITORIAL USE ONLY. NOT FOR SALE FOR MARKETING OR ADVERTISING CAMPAIGNS. THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS
ቁስለኛዉምስል Reuters
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ