1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶርያና የአውሮጳ ህብረት ማዕቀብ

ረቡዕ፣ የካቲት 21 2004

የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገሮች የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ትናንት ባካሄዱት ስብሰባቸው በሶርያ መንግሥት ላይ ተጨማሪ የኤኮኖሚ ማዕቀብ፡ በሶርያ ባለሥልጣናትም ላይህብረቱ ካሁን ቀደም በአንድ መቶ ሠላሣ ስምንት ሰዎችና ድርጅቶች ንብረት እንዳይንቀሳቀስ

https://p.dw.com/p/14BX6
ምስል AP


የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገሮች የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ትናንት ባካሄዱት ስብሰባቸው በሶርያ መንግሥት ላይ ተጨማሪ የኤኮኖሚ ማዕቀብ፡ በሶርያ ባለሥልጣናትም ላይህብረቱ ካሁን ቀደም በአንድ መቶ ሠላሣ ስምንት ሰዎችና ድርጅቶች ንብረት እንዳይንቀሳቀስ የጣለው ማዕቀብ እንደጸና የሚቆይ ሲሆን፡ አዲሱ ማዕቀብከሶርያ ጋ በወርቅና በከበሩ ደንጊያዎች ንግድ እንዳይካሄድ ፡ የዕቃ ማጓጓዣ አውሮፕላኖች ወደ ህብረቱ ሀገሮች እንዳይገቡ ወይንም ከህብረቱ ሀገሮች ተመሳሳይ ጉዞ ወደ ሶርያ እንዳይደረግ ያዛል።

በሌላ በኩል በሶርያ አስተዳደር ላይ የሚደረገው ጫናና ማዕቀብ ፕሬዚደንት በሽር አል አሳድን እስከሚያንበረክክ ምን ያህል ጊዜ ይፈጅ ይሆን?- የሚለዉ የብዙዎች ጥያቄ ነው። የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ያስፐር ባርንበርግ ያነጋገራቸው የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ፖለቲከኛ -ሮልፍ ሙንስኒሽ ጀርመን ከሩስያ ጋ ባላት ግንኙነት በመጠቀም ይህችው ሀገር ዓለም አቀፉ ማህበረ ሰብ በሶርያ መንግሥት ላይ የሚወስደውን ውሳኔ ትደግፍ ዘንድ እንድታግባባ ጠይቀዋል።

ገበያው ንጉሤ

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ