1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶርያና የጀርመን ሚና

ማክሰኞ፣ ጥር 28 2005

የባሽር አል አሳድ የአመራር ዘመን የተቆጠረ ነው ተብሎ ነበር። ይሁንና የመጀመሪያው ተቃውሞ ከተሰማ ከሁለት አመት ግድምም በኋላ ፕሬዚዳንቱ በስልጣን ላይ ናቸው። በዚህ መሀል ታድያ ጥያቄው ጀርመን እንደ አንድ ሀገር የሶሪያውን ቀውስ ለመፍታት ምን አይነት ሚና ልትጫወት ትችላለችየሚለው ነው።

https://p.dw.com/p/17Xwk
A Free Syrian Army fighter fires his rifle inside a Syrian Army base during heavy fighting in the Arabeen neighbourhood of Damascus February 3, 2013. REUTERS/Goran Tomasevic (SYRIA - Tags: CIVIL UNREST POLITICS)
ምስል Reuters

ደቡባዊው ጀርመን ውስጥ ሲካሄድ የሰነበተውና ትናንት በተጠናቀቀው 49ኛው የሚዩኒክ ዓመታዊ ዓለምአቀፍ የጸጥታ ጉባዔ ላይም ሶርያ ርዕስ ነበረች። በሶሪያ የመንግስት ወታደሮች እና ተቃዋሚዎች መካከል በመካሄድ ላይ ያለው ትግል ፍፃሜ አለማግኘቱን አንስተው የፖለቲካ እና የጦር ባለስልጣናት ሲመክሩበት ቆይተዋል።

በርስ በርስ ጦርነቱ 60 000 ሰዎች እስካሁን ሞተዋል። ከሁለት ሚሊዮን የሚበልጠው ህዝብ ደግሞ ከመኖሪያው ብሎም ከሀገሩ ተፈናቅሏል። በቱርክ ፣ በዮርዳኖስ፣ በኢራቅ እና ሊባኖስ 600 000 የሶሪያ ስደተኞች ይገኛሉ። እንደ ተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በምህፃሩ UNHCR መዘርዝር በየቀኑ ከሶርያ 2000-3000 ሶሪያውያን ከአገራቸው ወደ ጎረቤት ሀገራት ይሰደዳሉ። ጦርነቱ መፍትሄ የሚያገኝበት ጊዜ አይታወቅም። ይልቁንስ የመንግስት ወታደሩም ይሁን መንግስት ተቃዋሚው በገንዘብ እና በመሣሪያ ከውጭ ሀገራት ይደገፋል። የተጣሉት ማዕቀቦች በሙሉ የጦር መሣሪያ ድጋፉን ሊያስቆሙ አልቻሉም። የሶሪያ ሁኔታ መፍትሄ ያጣበት አንዱ ምክንያት ይላሉ፤ መንግስታዊ ካልሆነው ድርጅት «ጄኖሳይድ አለርት » ሮበርት ሹተ፤ « ወደ አንድ የታጠቁ ቀውስ ወደሚያካሂዱበት አካባቢ የጦር መሳሪያ መላኩ ጊዜ ተወስዶ የታሰበት አለመሆንን መረዳት ይኖርብናል። መሳሪያዎች አንዴ በእንደዚህ አካባቢዎች ከደረሱ መልሶ በቁጥጥር ስር ለማድረግ አዳጋች ነው። በፍጥነት ወደ ሌሎች የጦርነት ቦታዎች የሚላኩበት ሁኔታ ይፈጠራል። »

A woman escorts her children safely through the rubble of their destroyed village. Ras al-Ain, Syria *** Deutsche Welle, Andreas Stahl, 21.12.2012, 13:39:21
ምስል DW/A. Stahl
A Free Syrian Army fighter runs for cover as he enters a Syrian Army base during heavy fighting in the Arabeen neighbourhood of Damascus February 3, 2013. REUTERS/Goran Tomasevic (SYRIA - Tags: CIVIL UNREST POLITICS)
ምስል Reuters

በትክክል ይህን በሊቢያ ለመታዘብ ተችሏል። የሙአመር አል ጋዳፊ መንግስት ሲገለበጥ የጋዳፊ ደጋፊዎች ለመንግስቱ ተቃዋሚዎች የተላኩትን መሳሪያዎች በመስረቅ እና በማሸሽ ኋላም ለአልቃይዳ ቅርብ የሆነውንና በማግሬብ ለማሊ አመፅ ተጠያቂ የሆነውን አማፂ ቡድን ለመደገፍ ተጠቅመውበታል። እንደዚህ አይነት ክስተቶችን ወደፊት ለመከላከል ርምጃ ያስፈልጋል ይላሉ በጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የሶሻል ዲሞክራቱ ፓርቲ የውጭ ፖለቲካ አመራር ቃል አቀባይ ሮልፍ ሙዑትሰኒሽ፤ « የበለጠ የትጥቅ ሽያጫችንን እንድንቆጣጠር ፣ በተለይ ደግሞ ርግጠኛ ባልሆንንበት ሰዓት ከዚህ የውጭ ሀገር ንግድ እንድንቆጠብ ይህን ርምጃ እንድንወስድ የሚያደርገን ይመስለኛል። »

የሶሪያን የትጥቅ ሽያጭ በተመለከተ ከአሁን በኋላ ለውጥም ቢደረግ መፍትሄ አይሆንም ይላሉ ሹተ። አክለውም ጀርመን ይበልጥ ተሳትፎዋን ልታጠናክር ትችላለች። ግዴታ በወታደራዊ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ለምሳሌ ጀርመን በኋላ ለፍርድ ቤት የሚሆኑ ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ ትችላለች ይላሉ።

ለሶሪያ መፍትሄ ለማግኘት ለጀርመን ብቻ ሳይሆን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብም ድንበሩ ዝግ ነው። በሶሪያ መንግስት ላይ የኃይል ርምጃ ለመጣል በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ልዑክ አማካኝነት የሚታሰብ ነው። ያለበለዚያ የጀርመን ጣልቃ ገብነትን ህጉ የማይፈቅደው እንደሆነ በኮሎኝ ዮንቨርሲቲ የጀርመን እና አለም አቀፋዊ የወንጀል ህግ ፕሮፌሰር ክላውስ ክሬስ ያስረዳሉ።

« ህጉን ተመርኩዘን ከሄድን የሚነሳው ጥያቄ፤ ፍፁም አስቸጋሪ ወይንም በሚያስፈራ ወቅት ያለ ፀጥታው ምክር ቤት ውክልና ርመጃ መወሰድ መቻሉ ነው። ያ ደግሞ በአለም አቀፍ ህግ ደንብ አከራካሪ ነው።»

አነ አልሜሊንግ

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ