1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶርያ ተቃዉሞ እና የኃይል ርምጃ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 26 2003

የሶርያ መንግስት ከህዝብ የተነሳበትን ተቃዉሞና አመፅ ለማብረድ ፖለቲካዊ መፍትሄ ከመሻት ይልቅ አፈናና ማሳደድን መምረጡ ዓለም ዓቀፍ ዉግዘትን እያሰከተለበት ነዉ።

https://p.dw.com/p/RM21
ምስል picture alliance/dpa

ሆኖም የፕሬዝደንት ባሽር አልአሳድ መንግስት በአገሬ ጉዳይ ጣልቃ አትግቡ በሚል በድርጊቱ ገፍቶበታል፤ በዚህ ርምጃዉም አመፅ ከተነሳ አንስቶ ከአምስት መቶ በላይ ዜጎች ህይወታቸዉን ማጣታቸዉ በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ መቁሰል መታሰራቸዉ፤ እንዲሁም አንዳንዶች የደረሱበት እንዳልታወቀ እየተነገረ ነዉ። ሌሎች በሺዎች የተቆጠሩ ደግሞ ወደጎረቤት ሊባኖስ ለስደት መዳረጋቸዉ ተሰምቷል።

ነብዩ ሲራክ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ