1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቀኝ አክራሪነት በጀርመን

ማክሰኞ፣ ኅዳር 11 2005

በወንጀሉ አፍቃሪ ናዚዎች መጠርጠራቸው ይፋ ከወጣበት ካለፈው አመት አንስቶ በጀርመን የቀኝ አክራሪዎች ጉዳይ እንዳነጋገረ ነው ። ፍሪድሪክ ኤበርት የተባለው የጥናት ተቋም ባለፈው ሳምንት ባወጣው ዘገባ በመላ ጀርመን የቀኝ አክራሪነት አስተሳሰብ እየጨመረ መምጣቱን ማመልከቱ ጉዳዩ ይበልጥ እንዲተኮርበት አድርጓል ።

https://p.dw.com/p/16mxQ
Rechtsradikale sammeln sich am Samstag (30.04.2011) unter einer Hochstraße in Bremen zu einem NPD-Aufmarsch durch den Stadtteil Neustadt der Hansestadt. An der Kundgebung nahmen knapp 200 Neonazis teil. Die rechtsradikale Partei will bei der Bremer Landtagswahl am 22. Mai ins Parlament einziehen. An der Gegendemo nahmen etwa 4000 Menschen teil. Foto: Ingo Wagner dpa/lni (Zu lni 0339 vom 30.04.2011)
ምስል picture-alliance/dpa
BERLIN, GERMANY - MAY 01: Sebastian Schmidtke, Chairman of the Berlin branch of the far-right NPD political party, speaks at an NPD rally on the eastern city outskirts on May Day on May 1, 2012 in Berlin, Germany. German lawmakers, following the revelation that two neo-Nazis of the NSU terror group had committed at least nine murders over a multi-year killing spree, are again seeking to ban the NPD. (Photo by Sean Gallup/Getty Images)
ምስል Getty Images
ARCHIV - Springerstiefel eines Teilnehmers einer Demonstration der rechten Szene, aufgenommen in Dortmund (Archivfoto vom 21.10.2000). Von 160 Neonazis, die seit Januar 2012 in Deutschland auf der Fahndungsliste standen, wurden 46 von Ermittlern geschnappt, berichtet die "Süddeutsche Zeitung" (Ausgabe vom Donnerstag, 15.03.2012) und beruft sich dabei auf Antworten der Bundesregierung auf eine parlamentarische Anfrage der Partei "Die Linke". Foto: Bernd Thissen dpa/lnw +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa

በጀርመን የቀኝ አክራሪነት አዝማሚያ ከቀድሞው እየተጠናከረ በመሄድ ላይ መሆኑን በቅርቡ ይፋ የሆነ አንድ ጥናት አስታውቋል ። እንደ ጥናቱ በተለይ በምሥራቅ ጀርመን የውጭ ዜጎች ጥላቻ ከቀድሞው አሁን ተባብሷል ። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።
ባለፉት 12 ዓመታት ጀርመን ውስጥ በ 9 የውጭ ዜጎችና በአንድ ፖሊስ ላይ የደረሱ ግድያዎች ፣ በህቡዕ ሲንቀሳቀስ በቆየ ቀኝ አክራሪው ቡድን መፈፀሙ አነጋግሮ ሳያበቃ በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት በጀርመን የቀኝ አክራሪነት አስተሳሰብ አራማጆች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን መጠቆሙ አሳስቧል ። ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር አቃቤ ህግ በ 10 ሩ ሰዎች ግድያ ከተጠረጠሩት ራሱን ብሔራዊ ሶሻሊስት ህብረት ብሎ የሚጠራው በህቡዕ የሚንቀሳቀሰው ቀኝ አክራሪ ቡድን አባላት መካከል በህይወት በምትገኘው ላይ በይፋ ክስ የመሰረተው ።  በወንጀሉ አፍቃሪ ናዚዎች መጠርጠራቸው ይፋ ከወጣበት ካለፈው አመት አንስቶ በጀርመን የቀኝ አክራሪዎች ጉዳይ እንዳነጋገረ ነው ። ፍሪድሪክ ኤበርት የተባለው የጥናት ተቋም ባለፈው ሳምንት ባወጣው ዘገባ በመላ ጀርመን የቀኝ አክራሪነት አስተሳሰብ እየጨመረ መምጣቱን
ማመልከቱ ጉዳዩ ይበልጥ እንዲተኮርበት አድርጓል ። የጥናቱ ውጤት እንዳመለከተው ድርጅቱ ከዛሬ 2 አመት በፊት የቀኝ አክራሪነት አዝማሚያ በጀርመን በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ካካሄደው ጥናት ውጤት ጋር በማነፃፀር እንዳቀረበው ያኔ በመላ ጀርመን ከመቶ ሲሰላ 8.1 የነበረው አሁን ወደ 9 በመቶ አድጓል ። እንደ ጥናቱ ይህ አዝማሚያም ከአካባቢ አካባቢ ይለያያል ። በተለይ በምዕራብ ጀርመን ግዛቶች የዛሬ 2 አመት ይታይ የነበረው አዝማሚያ እጅግ በመጠኑ አነስተኛ መቀነስ ሲያሳይም በምሥራቁ ክፍል ግን እጅግ ከፍ ብሎ ተገኝቷል ። ከ 10.5 ወደ 15.8 አድጓል ። ይህም እንደ ተቋሙ እስካሁን በተካሄዱት ጥናቶች ከተገኘው ውጤት ከፍተኛው ነው የፍሪድሪሽ ኤበርት ጥናት ተቋሙ ባልደረባ ራልፍ ሜልትዘር በተለይ በምሥራቅ ጀርመን የቀኝ አክራሪነት ስሜት እየተስፋፋ የመጣበትን ምክንያት ከህዝቡ የኑሮ ሁኔታ ጋር ያያይዙታል ። ችግሩን መከላከል እንደሚገባም ያሳስባሉ  ።« እኛ በተለይ እንደምንገምተው ከሆነ በምሥራቁ ጀርመን ፌደራል ክፍላተ ሃገር አንዳንድ ተስፋ የቆረጡ ሰዎች የሚገኙባቸው አካባቢዎች አሉ ። ይህ የሚታየው ችግርም ሆነ ይሽው ዘረኝነት በጣም ተጠናክሮ የሚንጸባረቅባቸውም እነዚሁ ናቸው ። ዴሞክራቲክ ፓርቲዎች የቀኝ አክራሪዎች አጀንዳዎች ቀስ በቀስ እየሰረጉ እንዳይገቡ በግልፅ ማከላከል አለባቸው ። በአካቢዎችን ቀበሌዎች ደረጃ በቀኝ አክራሪዎችና በዴሞክራቲክ ፓርቲዎች ፖለቲከኞች መካከል የተቀራረበ ግንኙነት የለም ። »
በጀርመን ዘረኝነትን መዋጋት አንዱ አላማው አድርጎ የሚንቀሳቀሰው ባቢሎን የተባለው  ድርጅት መሪ ዶክተር መኮንን ሽፈራው በምስራቅ ጀርመን ቀኝ አክራሪነት ለመስፋፋቱ ምክንያቱ ተደጋግሞ እንደሚነሳው የሥራ አጡ ቁጥር በመጨመሩ ብቻ አይደለም ይላሉ ።

አቶ ዮናስ ለማ ጀርመን ሲኖር 27 አመቱ ነው ። ምስራቅ ጀርመን ኖሯል ። በጀርመን ዘረኝነት ጎልቶ መታየት የጀመረው ከውህደቱ በኋላ መሆኑን ይናገራል ። ሆኖም በዚህ ዘመን ዘረኝነት ጊዜ ያለፈበት አስተሳሰብ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ባይ ነው ። እንደ ዶክተር መኮንን ሽፈራው በጀርመን ዘረኝነትን ለመዋጋት ቁልፉ መሣሪያ ትምህርት ነው ። ይህ ውጤታማ መሆኑን የራሳቸውን ድርጅት እንቅስቃሴ በምሳሌነት በማንሳት ያስረዳሉ ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ