1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካው ትኩሳት ሁከት እንዳያስነሳ ተሰግቷል

ቅዳሜ፣ መስከረም 13 2010

የኬንያ የተቃዋሚዎች ጥምረት ባለፈው ነሐሴ 2 ቀን 2009 ዓ.ም በሀገሪቱ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ያቀረቡትን አቤቱታ የተመለከተው የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫው ውጤት ውድቅ እንዲደረግ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ ፍርድ ቤቱ ድጋሚ ምርጫ በ60 ቀናት ውስጥ እንዲካሄድ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር፡፡

https://p.dw.com/p/2kZWq
Kenia PK Raila Odinga zur Wahlniederlage
ምስል Reuters/T. Mukoya

የፖለቲካው ትኩሳት ሁከት እንዳያስነሳ ተሰግቷል

በራይላ ኦዲንጋ የሚመራው የተቃዋሚዎች ጥምረት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ቢያወድስም ለጥቅምት 16 ቀን ከተቆረጠለት ድጋሚ ምርጫ በፊት በምርጫ አስፈጻሚው በኩል መስተካከል ይገባቸዋል ያላቸው ጉዳዮች ካልተደረጉ በምርጫው ላይሳተፍ እንደሚችል አስጠንቅቋል፡፡ በስልጣን ላይ ያሉት የፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ ቀንደኛ ተፎካካሪ ራይላ ኦዲንጋ ትላንት ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስም ይህንኑ ማስጠንቀቂያ ደግመውታል፡፡ ሳምንታዊው “ትኩረት በአፍሪቃ” ዝግጅታችን አወዛጋቢውን የኬንያን ምርጫ ጉዳይ በዋናነት ይመለከታል፡፡ የቶጎ መንግስት ህገመንግስቱን ለማሻሻል በመሞከሩ የተቀሰቀሰበትን ተቃውሞም በአጭሩ ይቃኛል፡፡ 

 

ገበያው ንጉሴ  

ተስፋለም ወልደየስ