1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቆይታ ከድምፃዊ እሱባለዉ ይታየዉ ጋር

እሑድ፣ ታኅሣሥ 8 2010

ሙዚቃ የጀመረዉ በልጅነት እድሜዉ ነዉ። በ 11 ዓመቱ።ከድምጻዊነቱ ባሻገር ግጥምና ዜማዎችን መስራት የጀመረዉም በዚሁ የልጅነት እድሜዉ  የህጻናትና ወጣቶች ትያትር ቤት ተቀጣሪ ሆኖ ነዉ።ለሙዚቃ ስራ  ጀማሪ ባይሆንም የመጀመሪያ የሙዚቃ አልበሙን «ትርታዬ » በሚል መጠሪያ በቅርቡ  ለአድማጭ ጀሮ አብቅቷል።

https://p.dw.com/p/2p2Kn
Cover Tiritaye Esubalew Yitayew

ቆይታ ከድምፃዊ እሱባለዉ ይታየዉ ጋር

«ትርታዬ» ሲል የሰየመው የመጀመሪያ አልበሙን ሲሠራ ከአምስት ዓመታት በላይ ፈጅቶበታል የዛሬው የመዝናኛ ዝግጅት እንግዳችን። ድምጻዊነቱን ገና ከልጅነቱ የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ሳለ ነው የጀመረው። በ«ትርታዬ» አልበም ያካተታቸው ግጥም እና ዜማዎቹን የደረሰውም ራሱ ነው።   ድምጻዊውን ፀሓይ ጫኔ አነጋግራ ቀጣዩን ዝግጅት አጠናቅራለች።

ፀሀይ ጫኔ

ነጋሽ መሀመድ