1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሊቢያ የቀጠለው ጥቃት እና የጀርመን አቋም

ሐሙስ፣ ሰኔ 2 2003

የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ኪዳን፥ ኔቶ የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊን መንግስት ለማስወገድ በሀገሪቱ የጀመረውን ያየር ጥቃት እንደሚቀጥል አስታወቀ። የኔቶ ዋና ጸሀፊ አንደርስ ፎኽ ራስሙሰን ጋዳፊ እንዳበቃላቸውም ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/RShb
ምስል AP

በሊቢያ ከብዙ ሳምንታት ወዲህ የቀጠለው የጦር ሂደት እስካሁን የተጠበቀውን ወጤት አለማምጣቱ ሲታይ ይህ የራስሙሰን አነጋገር ብሩህ ሊመስል ይችላል። በሊቢያ ተልዕኮ መሪ ሚና የያዙት የኔቶ አባል ሀገሮች በወታደራዊው ርምጃ ላይ ከሌሎቹ አቻዎቻቸው ተጨማሪ ጠይቀዋል፤ ጀርመን ግን ይህን ዓይነት ተሳትፎ እንደማታደርግ የሀገሪቱ መከላከያ ሚንስትር ቶማስ ደ ሜዚየር በድጋሚ ግልጽ አድርገዋል።

ክርስቶፍ ፕርስል

አርያም ተኬሌ

ነጋሽ መሐመድ