1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእግር ኳስ ግጭት በመቀሌ

እሑድ፣ ግንቦት 6 2009

ትናንት በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ስቴዲዮም በነበረ የእግር ኳስ ግጥሚያ ግጭት መፈጠሩ ተሰምቷል ። የእግር ኳስ ጨዋታው የመቀሌ ከነማ እና የባህርዳር ከነማ በብሔራዊ ሊግ የሚያካሂዱት መደበኛ ግጥሚያ ነበር።

https://p.dw.com/p/2cx8j
Äthiopien Stadansicht Mek' ele
ምስል DW/Y. G. Egziabhare

ግጭቱ የተቀሰቀሰው ግጥሚያው በመካሄድ ላይ እያለ እንደነበር የአይን እማኞች ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል። ግጭቱን ለማስቆም ጣልቃ የገባው ፖሊስ አስለቃሽ ጪስ መተኮሱን እና ተመልካቾች መደብደባቸውን የዓይን እማኞቹ ይናገራሉ። በዚህም መሠረት ጨዋታው ሳይጠናቀቅ ታዳሚው ተበትኗል። ያነጋገርናቸው ሁለት የዓይን እማኞች የገለፁልንን ከዚህ በታች ተጭነው ሊያዳምጡ ይችላሉ። በጉዳዮ ላይ የትግራይ ክልል ፖሊስን እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም።

ልደት አበበ

ተስፋለም ወልደየስ