በማድመጥ መማር-የአድማጮች አስተያየት | በማ ድመጥ መማር | DW | 12.12.2008

በማ ድመጥ መማር

በማድመጥ መማር-የአድማጮች አስተያየት

ሥለ በማድመጥ መማር በመላዉ አፍሪቃ የሚገኙ አድማጮች ከሰጧቸዉ አስተያየቶች ጥቂቱን ያንብቡ።

DW

«ዶቸ ቬለ ራዲዮ በጣም ጥሩ ዝግጅቶች አሉት።በማድመጥ መማር ዝግጅት ደግሞ በጣም ተስማምቶናል።ይሕን በመሰሉት ዝግጅቶቻችሁ ግፉበት።»
(ከኢትዮጵያ)

«የተወደዳችሁ ዶቼ ቬለዎች ሥለ ዝግጅታችሁ ያለኝን ከፍተኛ አድናቆት ልገልፅላችሁ እወዳለሁ።-በተለይ ለ-በማድመጥ መማር።ይሕን ዝግጅት በጣም ነዉ-የምወደዉ።ባጭሩ በጣም ጥሩ ዝግጅት ነዉ።እዚሕ ያለነዉ ወደነዋል።ከዝግጅቱ ብዙ ተምረናል።የተወደዳችሁ ዶቼ ቬለዎች በዚሁ ቀጥሉበት።እኛም ይሕን ዝግጅት በተመስጦ እናደመጠዋለን።»
(ከሳዑዲ አረቢያ)


«በማድመጥ መማር የሚቀርበዉ አዲስ ተከታታይ ድራማ በጣም ተገቢ እንደሆነ ይሰማኛል።ምክንያቱም ከሌሎች የአፍሪቃ ሐገራት ጋር ሲነፃፀር ሐገራችን አንጎላ ሐብታም ብትሆንም እዚሕ ከፍተኛ የከባቢ ሐብት ጥፋት አጋጥሞናልና።ትምሕርት (የችግር መፍቻ) ቁልፍ እንደሆነ ተገንዝቤያለሁ።የተማሩ ወጣቶች አሉ ማለት መጪዉ ዘመን ካስተማማኝ እጅ ነዉ ማለት ነዉ።
(ፊጉይሬዶ ካሲንዳ፥ ከሁዋምቦ፥ አንጎላ)

«ሰዎች ባሕር ዉስጥ የሚጥሉት ቁሻሻ ሥለሚያስከትለዉ ብክለት የዳሰሰዉን ርዕስ በጣም ወድጄዋለሁ። ጉዳዩ የአፍሪቃ አሐጉርን ክፉኛ ከሚጎዱ ዋና ዋና ችግሮች አንዱ ነዉ።ሳሆቶሜና ፕሪቺፔም የዚሁ መጥፎ ችግር ተካፋይ ናት።መልዕክቱን በተለይ በአፍሪቃዉያን ዘንድ ይበልጥ ለማስረፅ በሚቀጥለዉ የበማድመጥ መማር ተከታታይ ዝግጅታችሁ ተመሳሳይ ጉዳዮችን ታነሳላችሁ የሚል ተስፋ አለኝ።»
(አዲልሰን ካስትሮ፥ ቡዶ-ቡዶ፥ ሳሆቶሜና ፕሪንችፔ)

«በማድመጥ መማር ዝግጅታችሁን አድምጬዋለሁ።በእዉነቱ በጣም ነዉ የወደድኩት።ሰዎች ለችግሮቻቸዉ ሁሉ የመንግሥታትን መፍትሔዎች ከመጠበቅ ይልቅ፥ የራሳቸዉን ችግር እራሳቸዉ መፍታት የሚችሉበትን ብልሐት የሚጠቁሙ ተጨማሪ ምክሮችን በሚቀጥሉት ዝግጅቶቻችሁ እንደምትሰጡ ተስፋ አደርጋለሁ።»
(ሳዲቅ መሐመድ ከናጄሪያ)

«የራዲዮ ድራማዎቹ በተለይ ደግሞ ሥለ ወጣትዋ አንጀሊና የሚያወሳዉ በጣም አስደስቶኛል።እንደዚያ አይነቱ ነገር እዚሕ ጊኒ-ቢሳዎም ይፈፀማል።እናቶች ሥለ ወሲብ ከሴት ልጆቻቸዉ ጋር ለመነጋገር ይፈራሉ።ልጆቹ ሥለ ወሲብ የሚያዉቁት ከዉጪ በመሆኑ ብዙ ጊዜ መጥፎ ሊሆን ይችላል።ጥሩ የመረጃ ልዉዉጥ የኤድስ ሥርጭትን ከመዋጊያ መንገዶች አንዱ ነዉ ብዬ አምናለሁ።እናንተ እያደረጋችሁ ያላችሁትም ይሕንኑ ነዉ።ለሥራችሁ አመሰግናለሁ።ትኩረት ያገኘ ጉዳይ ነዉ።»
(ዲያማንቲኖ ማሪያ ዳ ሲልቫ፥ ጊኒ ቢሳዎ)

«ሥለ ኤች አይ ቪ-ኤድስ የቃኘዉ ዝግጅት ሥለአኗኗራችን፥ ልጃገረዶችን እንዴት እንደምንይዛቸዉ፥ እና እነሱን ሥናታልላቸዉ አንዳዴ ሥለሚፈጠረዉ ችግር እንዳዉቅ አይኔን ከፍቶልኛል።ልጃገረዶች የሚወድቁበትን ወጥመድም እንድረዳ አድርጎኛል።ጉዳዩ እንደተለመደ ነገር መታየቱ ጥሩ ነዉ መባሉን አልቀበለዉም።የበማድመጥ መማር ገፀ-ባሕሪያት አቀራረብ ማራኪ ነዉ-ፊልም የመመልከት ያሕል ነዉ።ለወደፊቱም እዚሕ ኬንያ የሚገኙ ወጣቶችን ችግር በቀጥታ ለማስወገድ የሚረዱ ዝግጅቶች እንደሚኖሯችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።»
(ዴኒስ ዶንጋ፥ ኬንያ)

Albanian Shqip

Amharic አማርኛ

Arabic العربية

Bengali বাংলা

Bosnian B/H/S

Bulgarian Български

Chinese (Simplified) 简

Chinese (Traditional) 繁

Croatian Hrvatski

Dari دری

English English

French Français

German Deutsch

Greek Ελληνικά

Hausa Hausa

Hindi हिन्दी

Indonesian Bahasa Indonesia

Kiswahili Kiswahili

Macedonian Македонски

Pashto پښتو

Persian فارسی

Polish Polski

Portuguese Português para África

Portuguese Português do Brasil

Romanian Română

Russian Русский

Serbian Српски/Srpski

Spanish Español

Turkish Türkçe

Ukrainian Українська

Urdu اردو