1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በምሥራቅ የዩክሬይን ከተማ በስሎቭያንስክ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 24 2006

የዩክሬይን መንግሥት ወታደሮች ስሎቫንስክን ፣ መነጠል ይፈልጋሉ ከሚባሉት መፍቀሬ- ሩሲያ ኃይሎች እጅ አስለቅቆ ለመቆጣጠር ወታደራዊ የማጥቃት ዘመቻ መክፈታቸውን ጊዜያዊው የሀገር አስተዳደር ሚንስትር አርሰን አባኮቭ ገለጡ።

https://p.dw.com/p/1BsHX
ምስል Getty Images

ምሥራቁ ዩክሬይን እንዲገነጠል የሚሹት ወገኖች በተጠቀሰችው ከተማ 2 ሄሊኮፕተሮች መትተው መጣላቸውንና ሁለቱም አብራሪዎች መሞታቸውን የዩክሬይን መከላከያ ሚንስቴር አስታውቋል።

የኪየቭ መንግሥት ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ወደ ስሎቫንስክ በማምራት ላይ መሆናቸውንና ወደ ከተማይቱ ሠርገው የገቡ ወታደሮች እንዳሉ፤ በተለያዩ ጣቢያዎችም ውጊያ መከፈቱን ፤ ቭላዲስላቭ በሚል የመጀመሪያ ስም የሚጠቀሱት የመፍቀሬ ሩሲያውያኑ ወታደራዊ ክንፍ ይፋ ቃል አቀባይ አስታወቀዋል።

ተክሌ የኋላ