1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሞያሌው ግጭት የባለስልጣናቱ እጅ

ሰኞ፣ ሐምሌ 23 2004

ደቡብ ኢትዮጵያ በኬንያ ጠረፍ አኳያ በምትገኘው ሞያሌ ውስጥ ረቡዕ(18.11.2004 ዓ. ም.)በተቀሰቀሰው ግጭት አንዳንድ የአካባቢው አስተዳደር አካላት እጃቸው እንደነበረበት ተገለፀ። ይህን የተነናገሩት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ባለስልጣኑ አቶ አበበ ወርቄ ዛሬ ለዶቸ ቬሌ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ነው።

https://p.dw.com/p/15gnP

በግጭቱ 18 ሰዎች መገደላቸው እና በሺዎች የሚቆጠሩት ወሰን አቋርጠው ወደ ኬንያ እንደሸሹ ተዘግቧል። እንደ በርካታ የዜና አውታሮች ገለፃ ከኬንያ ድንበር 1 ነጥብ 6 ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኘው ሞያሌ ተቀስቅሶ የነበረው ግጭት ጋሪ እና ቦረና በተሰኙት ሁለት ጎሳዎች የመሬት ባለቤትነት ውዝግብ ሳቢያ ነበር የተነሳው።

የተለያዩ የዜና አውታሮች በግጭቱ 18 ሰዎች ተገድለው 12 መቁሰላቸውን እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩት መሰደዳቸውን መዘገባቸው ይታወቃል። በሁለቱ ጎሳዎች መካከል የተነሳው የመሬት የይገባኛል ጥያቄ አዲስ ሳይሆን ቆየት ያለ እንደሆነ ነው የሚነገረው። እንዲያም ሆኖ ግን የጎሳ አባላቱ ለረዥም ጊዜያት ጥይት ሲያከማቹ እና መሳሪያ ሲሰበስቡ ያስቆማቸው ሀይል አልነበረም ይላሉ የአካባቢው ነዋሪ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ