1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሞያሌ ኮሌራ ወይስ አጣዳፊ ተቅማጥ ?

ማክሰኞ፣ መጋቢት 8 2001

በኢትዮጵያ እና ኬንያ መሀል በምትገኘው የድንበር ከተማ ሞያሌ የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱንና በበሽታውም ሰዎች መሞታቸውን አንዳንድ የዜና ምንጮች እየዘገቡ ነው ።

https://p.dw.com/p/HEFr
የኮሌራ ተህዋስያን

ስለኮሌራው ወረረሽኝ ከዘገቡት አንዱ ኢሪን የተባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዜና አገልግሎት ሲሆን ዜና አገልግሎቱ የሞያሌ ሆስፒታል የጤና ባለሞያን ጠቅሶ እንደዘገበው በኮሌራ አስራ አራት ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን ሞተዋል ። ስለሞያሌው የኮሌራ ወረርሽኝ ዶይቼቬለ የአማርኛው ክፍል ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለስልጣን ግን በድንበር አካባቢ የተከሰተው ከፍተኛ ትኩሳት የታከለበት አጣዳፊ ተቅማጥና ተውከት እንጂ ኮሌራ ለመሆኑ ማረጋገጫ የለም ብለዋል ። ዝርዝሩን ታደሰ ዕንግዳው ከአዲስ አበባ ልኮልናል ።