1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሣዑዲ ዓረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሮሮ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 15 2006

የሃላፊዎች ሙሉ ቀን መጥፋት ያበሳጫቸው ነዋሪዎች ከቀትር በኋላ በነፍሰ ጡር እና በህጻናት ላይ እያደረሰ ያለው መንገላታት እየጎዳቸው መሆኑን በመግለጽ ለሶስት ሰአታት ተቃውሞ አሰምተው ነበር ።

https://p.dw.com/p/1AgVk
ምስል AFP/Getty Images

«ሕጋዊ ሰነድ የማታሟሉ ወደ ሃገር ቤት ግቡ! " በሚል የጅዳ ቆንስል ካወጣውን ተደጋጋሚ መረጃ በኋላ ከአምስት ቀናት ጅምሮ ወደ ሽሜሲ መጠለያ በአስር አውቶቡስ የገቡ ኢትዮጵያውያን ሰነድ ሳይሰረላቸው ለቀናት ሜዳ ላይ መንገላታታቸውን ሲያማርሩ ሰንብተዋል። የሃላፊዎች ሙሉ ቀን መጥፋት ያበሳጫቸው ነዋሪዎች ከቀትር በኋላ በነፍሰ ጡር እና በህጻናት ላይ እያደረሰ ያለው መንገላታት እየጎዳቸው መሆኑን በመግለጽ ለሶስት ሰአታት ተቃውሞ አሰምተው ነበር ። የሳዑዲ ጸጥታ አስከባሪዎች እሁድ እኩለ ሌሊት አመጽ ያነሱትን ከቦታው ለማስነሳት በወሰዱት ርምጃ በርካታ ኢትዮጵያውያን በድብደባው ጉዳት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። ስለሁከቱና በሁከቱ ጉዳት ደረሰብን የሚሉ ወገኖችን አነጋግሮ ነቢዩ ሲራከ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

ነቢዩ ሲራክ
ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ