1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሥጋት የተዋጠው መጪው የብሩንዲ ምርጫ

ዓርብ፣ መጋቢት 4 2007

ቡሩንዲ አጠቃላይ ምርጫ ልታካሂድ ጥቂት ወራት ቀር ቷት ሳለ ፣ ከወዲሁ ፍርሃት የነገሠ መስሏል። ፕሬዚዳንት ፒዬር እንኩሩንዚዛን የሚተቹ በየጊዜው የግድያ ዛቻ እንደሚሰነዘርባቸው ይነገራል።

https://p.dw.com/p/1EqVf
ምስል picture-alliance/Philipp Ziser

የቡሩንዲ ሕገ መንግሥት እንደሚለው አንድ ፕሬዚዳንት ከ 2 ጊዜ በላይ ፤ የአገልግሎት ዘመን በኋላ በሥልጣን ሊቆይ አይገባውም። እንኩሩንዚዛ ግን ለ3ኛ ጊዜ እጩ ሆነው ለመቅረብ ነው የተዘጋጁት። ይህ ዓይነቱን ሕገ ወጥ አካሄድ ከተቃወሙት መካከል የአገሪቱ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲንም ትገኝበታለች። በሥጋት ስለተዋጠው የቡሩንዲ የምርጫ ዝግጅት ----

Pierre Nkurunziza
ምስል I.Sanogo/AFP/GettyImages

ግንቦት 18 የሕዝብ እንደራሴዊዎች ፣ ሰኔ 19 , 2007 ደግሞ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንዲካሄድ ቀነ ቀጠሮ ተይዟል። ባለፈው ሳምንት፤ሐሙስ ፣ የአውሮፓው ሕብረት ዲፕሎማቶች፤ ከሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው በተነጋገሩበት ወቅት፤ የእንኩሩንዚዛ ፣ ለ 3ኛ ጊዜ እጩ ሆኖ ለመቅረብ መዘጋጀት፤ አደገኛ ውጥረት እንደሚያስከትል ለቡና አምራቺቱ፣ የ 10 ሚሊዮን ዜጎች ሀገር መረጋጋትም አስከፊ ሁኔታ ሊያስከትል እንደሚችል ነው ያስገነዘቡት። ፈላጭ ቆራጩ መሪ ለ 3ኛ ጊዜ የሥልጣን ጊዜ ለማራዘም ታጥቀው መነሳታቸውን የሚተቹ ወገኖች ፣ ተደጋጋሚ ዛቻ እንደሚሰነዘርባቸው ብቻ አይደለም የተነገረው። እንዲያውም ሊገደሉ ይገባል ተብለው ስማቸው በዝርዝር የቀረበ ስለመኖሩም ነው የሚወራው። APRODH በሚል ምሕጻር የተጠሰቀው የሰብአዊ መብት ጥበቃ ድርጅት ሊቀመንበር ፒዪር ክላቨር እምቦኒምፓ፣

«እንደተነገረን ከሆነ፣ የ RPA ራዲዮ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቦብ ሩጉሪካን ለመግደል እቅድ አለ።ዝርዝሩ ውስጥ የኔም ስም አለበት፤ እንዲሁም FOCODE የተባለው ፓርቲ አባል ፓስፊክ ኒኒናሐዝዌ ! በአንድ ግለሰብ ቤት ይህ ነገር ሲዶለት የብሔራዊው የስለላ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅም ተገኝተው ነበር።»

የአፍሪቃ ሕዝብ ራዲዮ ( RPA) የተሰኘውን ድርጅት ጋዜጠኛ ለመግደል እቅድ አለ ብሎ ለመናገር ምን ዓይነት ማስረጃ ይገኛል? የመንግሥት ቃል አቀባይ ቴሌስፎር ቢግሪማና ተከታዩን ቃል ሠንዝረዋል።

«የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነው አከብረዋለሁ። በዝች አገር እንደሚኖሩት ብዙዎቹ ዜጎች ሁሉ!ነገር ግን ማረጋጋጫ ማቅረብ የማይችልበትን ጉዳይ እያነሳ የመናገር መብት የለውም። የስም ዝርዝር አለ ካሉ አቅርበው ማሳየት ይኖርባቸዋል። »

የቡሩንዲ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መሪ ሊቀ ጳጳስ ኤቫርስቴ እንጎያጎዬ፤ ባሰሙት ተግሳጽ፤ «በሥልጣን ላይ የምትገኙ ሁሉ፣ አንድ ነገር ይከናወናል የሚል እንዲሁ ትንበያ መሰል ነገር ማሰማትም ሆነ ሕገ መንግሥቱን በተሳሳተ መልኩ ተርጉሞ ማቅረብ ተገቢ አይደለምና አደብ እንድትገዙ እንመክራለን፤ ሕገ መንግሥቱ እንደሁ ስለፕሬዚዳንቱ የአገልግሎት ዘመን በሚገባ በማያሻማ ቋንቋ ገልጿል። ማንም ፕሬዚዳንት፤ አምስት አምስት ዓመት ከ 2 የአገልግሎት ዘመን በላይ በሥልጣን ላይ መቆየት የለበትም » ነው የሚለው ሲሉ አስረድተዋል።

Bob Rugurika Journalist aus Burundi
ምስል Radio Publique Africaine

እ ጎ አ በ 2000 ዓ ም፤ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ኀላፊዎች ሁሉ ለሀገሪቱ ይበጃል ያሉትን የሰላም ውል ሲፈርሙ፤ የሚመረጥ ፕሬዚዳንት ከ 2 የአገልግሎት ዘመን በላይ ሥልጣን ላይ እንዳይቆይ መስማማታቸውን ጭምር ነው ሊቀ ጳጳሱ ያስታወሱት። 70 ከመቶ ገደማ የሆነውን ሕዝብ የምትወክለው ቤተ ክርስቲያናቸው ፤ በቡሩንዲ ለሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ፤ በቅርቡ ፣ የ 9 ቀናት ሥርዓተ ጸሎት፣ በሀገሪቱ በመላ እንደሚካሄድም ነው የተገለጸው። የሕዝቡ ሥጋት በግልጽ በመታየት ላይ መሆኑ አላጠራጠረም። የመንግሥት ቃል አቀባይ ቢጊሪማና ግን ይህ የሚያስገርም አይደለም ባይ ናቸው።

«ሕዝቡ ፍርሃት ቢያድርበት የተለመደ ነው። እንደምናውቀው፤ የቡሩንዲ ሕዝብ ከምጫ በፊት፤ ሁልጊዜ፤ በአጠቃላይ፣ ድንጋጤ አይታይበትም። ይሁንና ሰዎች የግል ዓላማቸውን ለማንጸባረቅ መሠረት የሌለው ጉዳይ መናገርም ሆነ መጻፍ አይኖርባቸውም ፣ አደገናኛ ነውና! »

ፕሬዚዳንት ፒየር እንኩሩንዚዛ ፣ የሆነው ሆኖ ግፊት እያየለባቸው ነው ፤ ከሕዝብ በኩል ያላቸው ድጋፍም እየተመናመነ መጥቷል። እ ጎ አ በ 2007 የፓርቲያቸው አባልና ሊቀመንበር የነበሩት ሁሴን ራጃቡ፤ አሁን ዋና ተፎካካሪአቸው ሆነው ይቀርባሉ። እንኩሩንዚዛ አስይዘው 13 ዓመት እሥራት ያስፈረዱባቸው ራጃቡ፤ ባለፈው ሰኞ አምልጠው በመጥፋት ወደ ውጭ ሀገር ሳይጓዙ አልቀሩም። ራጃቡ በህዝብ የተወደዱ መሆናቸው ነው የሚነገርላቸው። በምርጫ ቢወዳዳደሩ ማሸነፍ የሚችሉ መሆናቸውም ይታሰባል። CNDD-FDD በሚል ምሕጻር የሚታwm,ቀው ፓርቲ ሊቀመንበር ራጃቡ እንዲህ ይላሉ።

«በሀገራችን ፣ የፀጥታው ይዞታ ተባብሶአል። በዚህ ቀውጢ ሰዓት በምርጫ በመሳተፍ ፣ ፖለቲካው ለሀገሪቱ ሰላም እንዲያመጣ አደርግ ዘንድ ተማጽኖ ቀርቦልኛል። »

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ