1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በርሊናሌ ፊልም ፌስቲቫል-ያልተጠበቀ ውጤት

ሰኞ፣ የካቲት 23 2001

ፊልሙ የዳኞችን አይን መሳብ ከቻለ የፊልሙ አዘጋጅ ወይንም ደራሲ፣ ተዋናይ አለያም የማጀቢያ ሙዚቃ አቀናባሪው በርሊን ከተማ ፌስቲቫሉ በሚከናወንበት አዳራሽ እንዲታደም ጥሪ ይደረግለታል ማለት ነው። ታዲያ ለአስር ተከታታይ ቀናት የጀርመን ቆይታው የአየር መጓጓዣውን ጨምሮ ወጪውን የሚችለው የፌስቲቫሉ አዘጋጅ ነው።

https://p.dw.com/p/Gz9H
ወርቃማው ድብ፣ የበርሊናሌ ሽልማት
ወርቃማው ድብ፣ የበርሊናሌ ሽልማትምስል AP

ከታዋቂ የሆሊውድ ብርቅዬ አርቲስቶች አንስቶ እስከ ታላላቅ የዓለማችን የፖለቲካ መሪዎች ተመላልሰውበታል፥ የበርሊኑ ቀይ ምንጣፍ። ለአስር ተከታታይ ቀናት በበርሊን ከተማ በደመቀ መልኩ ሲከበር ቆይቶ ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀው በርሊናሌ ፊልም ፌስቲቫል በስተመጨረሻ አስደናቂ ሆኖ ነበር የዋለው። በፊልሙ ዓለም ፈፅሞ የማትታወቀው የፔሩ ተወላጅ ሴት የፊልም ዳይሬክተር ክላውዲያ ሎዛ ቀዩ ምንጣፍ ላይ በብቸኝነት ተራምዳለች። በደመቀ ጭብጨባ ታጅባም “La Teta Asustada” “የወተት ሀዘን” በሚል ርዕስ ያቀረበችው ፊልሟ በአንደኝነት ተመርጦ ተሸላሚ አድርጓታል።

Sileshi,Mantegaftot,Negash Mohammed

ZPR,Agenturen