1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሰዉ እጅ የተገደለዉ ኤርትራዊ ጉዳይ

ዓርብ፣ ጥር 15 2007

ብዙዉን ሰዉ እዚህ ያነጋገረዉ ጉዳይ ተጣርቶ መልስ ያገኘ ይመስላል ይላል የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤን በላከልን ዘገባ። ጋዜጣዎች ጽፈዋል፤ ሰዎች ሰልፍ ወጥተዋል እኛም ይላል ይልማ የኤርትራዊዉን ስደተኛ የወጣት ካሊድን ጉዳይ አንስተን ዘግበናል።

https://p.dw.com/p/1EPhe
Dresden Gedenkmarsch Mord Asylbewerber 17.01.2015
ምስል picture-alliance/dpa/O. Killig/

በብዙዎች የተገመተዉ በዉጭ ሀገር ዜጋ ላይ ጥላቻ ያሳያሉ የሚባሉት ወገኖች ከሀገሩ ከተሰደደ ብዙም ወራት ያልሆነዉን ኤርትራዊ ሕይወት ቀጥፈዉ ይሆናል የሚል ነበር። ይህም ነዉ ዘረኝነት የሚያሳዩ ወገኖቻቸዉን ተቃዉመዉ አደባባይ የወጡ ጀርመናዉያን ሳይቀሩ ፎቶዉን ይዘዉ ፍትህ እንዲያገኝ ድምፃቸዉን እንዲያሰሙ ያደረጋቸዉ። የፖሊስ ምርመራ ግን ያመላከተዉ ሌላ ነዉ። በምሥራቅ የጀርመን ግዛት ድሬዝደን ከተማ በሰዉ እጅ ሕይወቱ ስላለፈችዉ ወጣቱ ስደተኛ ካሊድ የአሟሟት ሁኔታ የተከታተለዉን ዘጋቢያችን ይልማ እንደሚከተለዉ አጠናቅሮ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ