1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሴቶች ግርዘት ላይ የጀርመን አቋም

ዓርብ፣ ጥር 29 2001

በጀርመን ህግ መሰረት ሴት ልጁን የሚያስገርዝ እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ዕስራት ይቀጣል ።

https://p.dw.com/p/Gomr
ምስል picture-alliance/ dpa
በጀርመን ህግ ላይ እንደሰፈረው የሴት ልጅን የመዋለጃ አካል መቁረጥ ማለት በጤናማ አካል ላይ አደጋ ማድረስ ነው ተብሎ ነው የሚታሰበው ። ከሴት ልጅ የመዋላጃ አካላት መቁረጥ ጋር የተያያዙ በርካታ አቤቱታዎች ጀርመን ፍርድ ቤቶች ይቀርባሉ ። ሆኖም ሁሉም ከበቂ ማስረጃ ጋር አልቀረቡም ። በዚህ የተነሳም ዳኞች ማን ድርጊቱን እንደፈፀመ እና ማን እንዳስፈፀመ ማረጋገጥ አልቻሉም ።