1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በስህተት የተገደለው ኢትዮጵያዊ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 19 2009

የሞገስ ስም በስህተት ከተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በመገኘቱ ወንድሙ እና ጓደኞቹ መንግሥት ፍትህ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው ።

https://p.dw.com/p/2c203
Fintech London | Skyline Finanzdistrikt
ምስል Sarah Bradbury

Beri London (Request for Justice for the death of an Ethiopian 27 years ago) - MP3-Stereo

           
ከዛሬ 27 ዓመት በፊት ለንደን ውስጥ የራሱን ህይወት አጥፍቷል የተባለ ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ፍትህ እንዲያገኝ ቤተሰቦቹ እና ወዳጆቹ በድጋሚ ጠየቁ ። የሟች ወንድም እንደሚሉት ፣ፖሊስ ሞገስ አባይ የተባለው ወንድማቸው በጎርጎሮሳዊው ሰኔ 30 1990 ከሚኖርበት ህንፃ ራሱን ወርውሮ ህይወቱን አጥፍቷል ቢልም በወቅቱ የተገኙት መረጃዎች ግን አጠራጣሪ ነበሩ ። የአይን ምስክሮችም ሆኑ የሟች ወንድም ሞገስ ያኔ  የራሱን ህይወት ማጥፋቱን የሚጠቁም ማስረጃ እንዳላዩ ነው የሚናገሩት ። በቅርቡ ደግሞ የሞገስ ስም በስህተት ከተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በመገኘቱ ወንድሙ እና ጓደኞቹ መንግሥት ፍትህ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ነው ። ዝርዝሩን የለንደንዋ ወኪላችን ሀና ደምሴ ልካልናለች ። 
ሀና ደምሴ 
ኂሩት መለሰ 
ነጋሽ መሐመድ