1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በስደተኞች ሰበብ የሻከረው የጀርመን እና የፈረንሳይ ግንኙነት

ረቡዕ፣ የካቲት 9 2008

የጀርመን መንግሥት ቃል አቀባይ ሽቴፈን ዛይበርት ሰሞኑን በበርሊን፣ የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዦን ማርክ ኤይሮሞ በብራስልስ ከሰኞ ዕለቱ የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ጉባዔ ላይ የአገሮቻቸውን ግንኙነት መልካም በሚል ሲያሞግሱ ተሰምተዋል። ይሁንና፣ ይህ ዓይነቱ ተደጋጋሚ ሙገሣ፣ ግንኙነቱ መበላሸቱን እንደሚጠቁም ታዛቢዎች ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/1Hwhw
München Sicherheitskonferenz - Manuel Valls
ምስል Reuters/M. Dalder

[No title]

በሚውኒክ፣ ጀርመን ባለፈው የሳምንት መጨረሻ በተካሄደው የፀጥታ ጉባዔ ላይ የተገኙት የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንስትር ማኑዌል ቫልስ በብዛት ወደ አውሮጳ የገቡትን ስደተኞች በመከፋፈሉ ጥያቄ ላይ የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ባቀረቡት ሀሳብ ላይ በፓሪስ እና በበርሊን መካከልትልቅ ልዩነት እንዳለ ካጎሉ በኋላ ነበር የሁለቱ ሀገራት ፖለቲከኞች የፈረንሳይ እና የጀርመንን ግንኙነት መልካምነት ያስታወቁት። ቫልስ ቀደም ሲል በሰጡት አንድ ቃለ ምልልስ የሜርክልን የስደተኞችን ፖሊሲ ለዘለቄታው ሊቀጥል እንደማይችል ነበር ያስታወቁት። በወቅቱ ይህንኑ የተገን አሰጣችን ጉዳይ በሚመለከት በወቅቱ አንድ የጋራ ፖሊሲ እንደሌለ በጀርመን ፌዴራዊ ምክር ቤት ፣ ቡንድስታኽ የክርስትያን ዴሞክራቶች ህብረት እንደራሴ አንድሪያስ ዩንግ በማስታወቅ መፍትሔ ሊገኝ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
« ለተቸገሩ ተገን መስጠት የጀርመናውያን መሰረታዊ ግዴታ ብቻ ሳይሆን፣ የአውሮጳውያንም መሰረታዊ እሴት ነው። አውሮጳ የቀኝ አክራሪዎችን በመፈፍራት ይህንኑ እሴቷን የምትተውበት አሰራር የተሳሳተ ይሆናል። ይህን ክስተት ጀርመን ውስጥ ብቻ ሳይሆን በፈረንሳይም እያየነው ነው። እና ፣ በተለይ በፈረንሳይ የሚገኘው ሶሻሊስታዊ መንግሥት ለዚሁ እሴት እንደሚቆም እና በመጨረሻም ለችግሩ በጋራ ባስቸኳይ አስፈላጊ የሆነውን አንድ መፍተትሔ እንደምናገኝለት ተስፋ አደርጋለሁ።»
የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔር እና መራሕያነ መንግሥት በነገው ዕለት በብራስልስ በሚያካሂዱት ጉባዔ ላይ የህብረቱን የውጭ ድንበር በማጠናከሩ እና ስደተኞቹን በመከፋፈሉ ሀሳብ ላይ አባል ሀገራት እንደሚቀራረቡ ተስፋ ቢያደርጉም፣ ይህ ገሀድ መሆኑን በጀርመን ፈረንሳይ የፖለቲካ ተቋም ባልደረባ አይሊን ተጠራጥረውታል።
« ጀርመን እና ፈረንሳይ ካልተስማሙ፣ ዋነኛ ውሳኔዎች መድረስ አዳጋች ነው። »
የህብረቱን የውጭ ድንበር ቁጥጥር ማጠናከሩ እና ወደ አህጉሩ የሚገቡትን ስደተኞች ቁጥር ለመቀነስ እንዲቻል ለቱርክ የፊናንስ ርዳታ ይሰጥ በሚለው ሀሳብ ላይ ሆኖም፣ ሁለቱ ሀገራት የያዙት ተቀራራቢ አመለካከት ገላጋይ ሀሳብ እንዲደረስ ይረዳ ይሆናል፣ ይላሉ አይሊን ኬለር። በአውሮጳ ምክር ቤት የተወከሉት ፈረንሳዊቷ የ«ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ» ፓርቲ እንደራሴ ሲልቪ ጉላር አስተያየት ግን ፣ ፈረንሳዊው ጠቅላይ ሚንስትር ቫልስ የመራሒተ መንግሥት ሜርክልን ጥያቄ በጀርመን ሀገር መቃወማቸው ትክክለኛ ሆኖ አላገኙትም።
« እንደማስታውሰው ፣ ድሮ ወጣት ሳለሁ በጀርመን እና በፈረንሳይ መካከል የሚፈጠሩ ችግሮች በሌላ ዘዴ ነበር የሚመከርባቸው። »
በዚህም የተነሳ ፓሪስ ጀርመንን እንዴት ልትረዳ እንደምትችል ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ማፈላለግ በተገባት ነበር ያሉት ሲልቪ ጉላር፣ አንጌላ ሜርክል የውጩ ድንበር ይከፈት በሚልበተናጠል የተከተሉት ፖሊሲአቸው በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ በወቅቱ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳረፉ እንደማይካድ አስታውቀዋል። ይሁንና፣ ይላሉ ሲልቪ ጉላር፣ የስደተኞቹ ቁጥር ሲቀንስ ግንኙነታቸው መሻሻሉ አይቀርም።

Slowenisch-österreichische Grenze Kinder Flüchtlinge
ምስል Reuters/L. Foeger
Andreas Jung Bundestag
ምስል Deutscher Bundestag/Achim Melde

ፔተር ሂለ/አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ