1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በስደተኞች ጉዳይ የአዉሮጳ ኅብረት አዲስ ሰነድ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 27 2008

የአዉሮጳ ኮሚሽን የስደተኞችን አቀባበልና አያያዝ በተመለከተ የተሻሻለ ነዉ ያለዉን አዲስ ሰነድ ትናንት በኅብረቱ ጽ/ቤት ይፋ አድርጎአል።

https://p.dw.com/p/1Iilt
ምስል picture alliance/abaca/AA

[No title]

ሰነዱ አባል ሃገሮች የጋራ የስደተኞች ፖሊስን እንዲከተሉ ኃላፊነትንና ወጭን እንዲጋሩ የሚያስገድድ ሲሆን አላማዉም ወደ አዉሮጳ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቀነስና በአዉሮጳ የሚታየዉን የስደተኞች ቀዉስ ለማቃለል እንደሆን ተመልክቶአል። ስደተኞችን መጀመርያ በገቡበት የኅብረቱ አባል ሃገር ጥገኝነት እንዲጠይቁ የሚያስገድደዉ የደብሊኑ ስምምነት በዚሁ አዲስ መመርያ የተሻለ ባይሆንም የሚስማማ አዲስ የአሰራር ስልት ተቀይሶአል ተብሎአል። አዲስን መመርያ ይፋ ያደጉት የኮሚሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት ፋራንስ ቲመርማንስ ከቱርክ ጋር የተደረሰዉ ስምምነት ዉጤት እያስገኘ መሆኑን ገልፀዋል። የቱርክ ዜጎች ወደ አዉሮጳ የሚገቡበትን አሰራር ኮሚሽኑ በሰነዱ ያካተተ መሆኑን አስታዉቀዋል።

ገበያዉ ንጉሴ


አዜብ ታደሰ