1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በስደት ህይወቱ ያለፈዉ ጋዜጠኛ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 5 2007

በቅርቡ ሐገሩን ጥሎ ወደ ኬንያ የተሰደደዉ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹርቤ ከትናንት በስተያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የጋዜጠኛ ሚሊዮን ባልደረቦች እና ጓደኞች እንደሚሉት ሚሊዮን ያረፈዉ ለሁለት ሳምንት ያሕል ከታመመ በሕዋላ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1DWBk
Trauer nach dem Amoklauf in Winnenden Baden Wuerttemberg
ምስል AP

ጋዜጠኛ ወደ ኬንያ የተሰደደዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ያሥረኛል ወይም ይከሰኛል በሚል ፍራቻ ነበር።

ተወልዶ ያደገው የጋዜጠኝነት ሥራውንም የጀመረው በይርጋጨፌ አካባቢ ነበር። ደቡባዊ-ኢትዮጵያ። በኢትኦጵ ጋዜጣና እና ቁም ነገር መጽሄት ላይም ሠርቷል-ጋዜጠኛሚሊዮንሹሩቤ። ላለፉት ሶስት አመታት ማራኪ የተሰኘ የግል ጋዜጣ በዋና ስራ አስኪያጅነት በመምራት ላይ የነበረው ሚሊዮን ጳጉሜ 5/2006 ዓ.ም. ወደ ኬንያ ከሌሎች አራት የሙያ ባልደረቦቹ ጋር መሰደዱን ጋዜጠኛ መላኩ አማረ ይናገራል። ኬንያ ሲደርስ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ጤነኛ ነበር የሚለው መላኩ ባለፉት 12 ቀናት ግን የጤና ሁኔታው በማሽቆልቆሉ ተደጋጋሚ ህክምና ለማግኘት ሞክሮ ነበር።ሚሊዮን ለሞት የተዳረገበት ምክንያት እስካሁን በግልጽ አልታወቀም። መላኩና በኬንያ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች አስከሬኑን በኢትዮጵያ በክብር ለማሳረፍ ሙከራ በማድረግ ላይ ናቸው። ጋዜጠኛ ሚሊዮን የአንዲት ታዳጊ ወጣት አባት ነበር።

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ