1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሶማሊያ የአሸባብ ታጣቂዎችን ጨምሮ ቢያንስ 22 ተገደሉ

እሑድ፣ ኅዳር 12 2008
https://p.dw.com/p/1HAMc
MQ-9 Reaper Drohne Drohnenkrieg Ziel Drohnenangriff Afghanistan
ምስል picture-alliance/AP/Air Force/L. Pratt

የአሸባብ ታጣቂዎችን ጨምሮ ቢያንስ 22 ሰዎች በተለያዩ ጥቃቶች ዛሬ መገደላቸውን ባለስልጣናት እና የዓይን እማኞች ገለጹ። ማዕከላዊ ሶማሊያ ውስጥ በሁለት የራስ ገዝ ግዛቶች ታጣቂዎች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ቢያንስ 14 ሰዎች ሲሞቱ 13 መቁሰላቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል። ተኩሱ የተካሄደው የፑንትላንድ እና ጋልሙዱግ ታጣቂዎች የጋልካዮን ከተማ ለመቆጣጠር ባደረጉት ውጊያ ነው።

ከዚህ ቀደም ብሎ የአሸባብ አባላትን መቀመጫ ኢላማ ያደረገ ሰው አልባ አይሮፕላን ደቡብ ሶማሊያ ውስጥ ቢያንስ 5 የቡድኑን አባላት እንደገደለ የሶማሊያ የስለላ ተቋም ለጀርመን ዜና ምንጭ ገልጿል። እንደ ስለላ ተቋሙ መረጃ ከሆነ ቅዳሜ ሌሊት ላይ ሶስት ሮኬቶች የቡድኑን መቀመጫ ደብድበዋል። ከሟቾቹ መካከል የአሸባብ ከፍተኛ አመራሮች ይገኙበታል ተብሏል። የሰው አልባ አይሮፕላን ምንጭ እስካሁን አልታወቀም። ይሁንና ዮናይትድ ስቴትስ የሶማሊያ መንግሥት ሸማቂ ቡድንን ለመዋጋት በሚያደርገው ተግባር ሰው አልባ አይሮፕላን በመጠቀም ድጋፍ መለገሷ ይታወሳል። አሸባብ እስካሁን ለዚህ ምላሽ አልሰጠም።

ልደት አበበ

እሸቴ በቀለ