1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሶማሊያ የጋዜጠኞች መገደል

ሰኞ፣ የካቲት 26 2004

ሶማሊያ ውስጥ በአራት ወር ውስጥ አራት ጋዜጠኞች ተገድለዋል። አራተኛው ጋዜጠኛ ትናንት ምሽት በተደጋጋሚ በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፋለች። የግድያው መንስኤ ምንድን ነው? ጋዜጠኞቹስ እነማን ናቸው?

https://p.dw.com/p/14FKx
ምስል Reuters

ሶማሊያ ውስጥ በአራት ወር ውስጥ አራት ጋዜጠኞች ተገድለዋል። አራተኛው ጋዜጠኛ ትናንት ምሽት በተደጋጋሚ በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፋለች። የአይን እማኞች እንደሚሉት የ24 አመቱ ጋዜጠኛ አሊ አህመድ አብዲ ወደ ቤቱ በሚመለስበት ሰዓት ነው መሳሪያ የታጠቁ ሁለት ሰዎች አስቁመው በተደጋጋሚ ወደ ጭንቅላቱ በመተኮስ የገደሉት። አስክሬኑም ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ተወሰደ። ወዴት? የታወቀ ነገር የለም። በአራት ወር ውስጥ አራት ጋዜጠኞች በሶማሊያ በተለያዩ ቦታዎች ተገድለዋል። « ስለ ግድያው አንድ ነገር ለማለት የሚያስችለን በይፋ ማንም የተያዘ ወይም ክስ የተመሰረተበት ሰው የለም።»

የዶይቸ ቬለ የሞቃዲሾ ዘጋቢ ሁሴን አወይስ።

በሶማሊያ ሰሜኒያዊው ክፍል ጋልካዮ ወረዳ ከተገደለው ጋዜጠኛ ውጪ ታጣቂዎች ከስድስት ቀን በፊት የሶማሊያውያን ሬዲዮ ኃላፊ- አቡካር ሀሳን ካዳፍን ገድለዋል። በጥር ወር ሻቤለ የተባለ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ከዚያ ቀደም ሲል በታህሳስ ወር ደግሞ ሞቃዲሾ ውስጥ እንዲሁ ሌላ ጋዜጠኛ ተገድሏል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ስለተገደሉት ጋዜጠኞች አዌይስ፤

«ሞቃዲሾ የተገደሉት ጋዜጠኞች ሶማሊያውያን ናቸው። በሞቃዲሾ እና በተለያዩ የሶማሊያ ክፍሎች የሚገኙ የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚያገለግሎ ጋዜጠኞች ናቸው።»

በሁለት ታጣቂዎች የተገደለው ጋዜጠኛ - አብዲ ለሶማሊያ ድረገፅ መስራት ከመጀመሩ አስቀድሞ ሬዲዮ ጋልካዮ ያገለግል ነበር። ግድያው ከተፈፀመ በኋላ ፖሊስ ምርመራውን ለማካሄዱ በቦታው ቢደርስም ታጣቂዎቹ ግድያውን ፈፅመው በፍጥነት ተሰውረዋል።

ድንበር አያግዴው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት -ሪፖርተርስ ውዝዓውት ቦርደርስ- ሶማሊያ በጋዜጠኞች ሞት ከአፍሪቃ ሀገሮች ግንባር ቀደም ቦታ የምትይዝ ሀገር ብሏታል። በሞቃዲሾ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ተሻሽሏል የሚል ነገር ይሰማ ነበር። ይሁን እና በፑትላንድ እና ሌሎች የሶማሊያ ክፍሎች አለመረጋጋት ይታያል። በአሁኑ ሰዓት በሶማሊያ ያለው የደህንነት ሁኔታ ምን ይመስላል? አዌይስ ሲመልስ፤

***Für mögliche Ergänzungen der Karte, wie z.B. andere Sprachen, zusätzliche Orte oder Markierungskreuz, wenden Sie sich bitte an infografik@dw-world.de (-2566), Außerhalb der Bürozeiten an bilder@dw-world.de (-2555).***
ሶማሊያ

« ከዚህ በፊት ስላለው ሁኔታ መናገር ይቻላል። አሸባብ ከሞቃዲሾ ሸሽቶ ወቷል። ይሁንና አሁንም አሸባብ በአንዳንድ ስፍራዎች የሚያካሂዳቸው ነገሮች አሉ። « አደጋ ጥሎ መሸሽ» የሚለውን የውጊያ ስልት ጀምሯል። ስለዚህ መተው ግድያ የሚፈፅሙበት ሁኔታ አለ። እና በአሁኑ ሰዓት ያለው የፀጥታ ሁኔታ በአጠቃላይ ጥሩ ነው ለማለት ያስቸግራል።»

አስቸጋሪ የሚያደርገው የፀጥታ ሁኔታው ብቻ ሳይሆን ከነዚህ ግድያዎች በስተጀርባ ከተጠርጣሪው አሸባብ ቡድን ሌላ እጅ ይኑርበት አይኑርበት አለመታዎቁ ነው። አሸባብ ስለግድያዎቹ ኃላፊነት ወስዶ ይፋ ያደረገው ነገር የለም።

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ