በሶማሊያ የፖለቲካ ሂደት የአሜሪካን ሚና
ሐሙስ፣ መስከረም 24 2005ማስታወቂያ
የአሜሪካን መንግሥት ሶማሊያ ራሱን የቻለ የመከላከያ ሠራዊት እንዲኖራት ለማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምትሰጥ አስታወቀ ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶማሊያ አምባሳደር በበኩላቸው የሶማሊያን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችለውን አስፈላጊውን እርዳታና ድጋፍ ለመቀበል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል ። የሶማሊያን ጉዳይ የሚከታተሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ደግሞ አሜሪካ በሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር የምትፈልገው ለራሷ ደህንነትና ጥቅም ስትል ነው ብለዋል ። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ቀጣዩን ዘገና ልኮልናል ።
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ