1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሶሪያ የቀጠለዉ ህዝባዊ አመፅ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 20 2003

በሶሪያ ህዝባዊዉ አመፅ ከተቀጣጠለበት ከመጋቢት ወር አጋማሽ አንስቶ ከስድስት መቶ ሰዎች በላይ ህይወት መቀጠፉን ዘገባዎች ያመለክታሉ።

https://p.dw.com/p/RKul
ምስል picture alliance/dpa

በፕሬዝደንት ባሽር አልአሳድ ላይ የተነሳዉ ተቃዉሞ በተጋጋለባት ደራ ከተማ ዉሃና የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡም ተነገሯል። በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የኃይል ርምጃ በሚሰነዝረዉ የሶርያ መንግስት ለድርጊቱ ዓለም ዓቀፍ ዉግዘት ቢገጥመዉም ትናንት በጉዳዩ ላይ የተነጋገረዉ የተመር የጸጥታዉ ምክር ቤት ግን በጋራ ድምፁን ለማሰማት አልተሳካለትም። ሩሲያ፤ ቻይና እና ሊባኖስ የሶርያ መንግስትን ድርጊት ለመቃወም አለመፈለጋቸዉን ሲያሳዩ፤ የአዉሪጳ ኅብረት ለብቻዉ በሶሪያ መንግስት ላይ ማዕቀብ የሚጥልበትን መንገድ እየቀየሰ መሆኑ ተገልጿል።

ነብዩ ሲራክ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ