1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሽብር ተጠርጣሪ ታሳሪዎች በነፃ እንዲሰናበቱ መወሰኑ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 14 2007

በፌደራል አቃቤ ሕግ በአሸባሪነት ክስ ተመስርቶባቸዉ የታሰሩት የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ«አንድነት» የሰማያዊና የአረና ፓርቲ አመራሮችና ሁለት ተጠርጣሪዎች በነጻ እንዲሰናበቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ወሰነ።

https://p.dw.com/p/1GJ5o
Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል AP

[No title]


ነጻ እንዲሰናበቱ ከተወሰነላቸዉ ከነዚሁ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች መካከል አንዱ ዛሬ እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተላልፏል ። ሶስቱ ግን ከዚህ ቀደም ችሎት በመድፈር የተላለፈባቸውን ቅጣት እንዳጠናቀቁ እንዲፈቱ ነው የተወሰነው። በሽብርተኝነት ክስ አንድ ዓመት ከአንድ ወር ግድም ታስረው ዛሬ በነፃ እንዲሰናበቱ የተበየነላቸው የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌዉና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፤ የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሺዋስ አሰፋና ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ናቸው።

በነጻ እንዲሰናበቱ የተወሰነውም በቀረበባቸዉን የሽብርተኝነት ክስ ከጥርጣሪ ባለፈ ተሳትፎአቸዉን ማረጋገጥ ባለመቻሉ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በዉሳኔዉ ማስታወቁ ተገልጿል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ታሳሪዎቹ ከእስር ቤት አልወጡም። የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉዓላዊነት ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት እንደሚሉት ፍርድ ቤቱ ከእስር እንዲወጡ ወስኖአል፤ ይወጣሉ የሚል ተስፋ አለን።

የፓርቲያችን ሥራ አስፈፃሚ አቶ አብረሃ ደስታ የሽብር ድርጊት ፈፅመዋል የሚል ፍፁም እምነት የለንም ያሉት አቶ ገብሩ አስራት በሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸዉ የታሰሩ ሁሉ እንዲለቀቁም ጠይቀዋል።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸዉ አንድ ሰዉ ይህን ያህል ጊዜ ለምን ይታሰራል ሲሉ ጠይቀዋል። እንዲለቀቁ የተፈረደላቸዉ እስረኞች እስር ላይ ሳሉ ችሎት በመድፈር በሚል ተከሰዉ ስለነበር ይዉጡ አይዉጡ ገና አልታወቀም ሲሉ ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት ተናግረዋል። ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።


አዜብ ታደሰ

Gericht Gesetz Jura Hammer Waage
ምስል fotolia/junial enterprises

ኂሩት መለሰ