1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቀድሞ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ የተላለፈው ብይን

ረቡዕ፣ ግንቦት 6 2006

ኦልሜርት ጉቦ በመቀበል በቀረቡባቸው በሁለት የክስ ጭብጦች ከ6 ሳምንታት በፊት የጥፋተኝነት ብይን ተላልፎባቸው ነበር ። ኦልሜርት ላይ ትናንት ውሳኔ የተላለፈው ለሁለት ዓመታት ከተካሄደ የፍርድ ሂደት በኋላ ነው ። ኦልሜርት 160 ሺህ ዶላር የሚደርስ ጉቦ ተቀብለዋል ሲል ፍርድ ቤቱ አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/1Bzjc
Israel Korruption Ehud Olmert 13. Mai 2014
ምስል Reuters

ትናንት ቴላቪቭ ውስጥ ያስቻለው የእስራኤል ፍርድ ቤት በቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሁድ ኦልሜርት ላይ የ6 ዓመት እስራትና የ290 ሺህ ዶላር ቅጣት በይኗል ። የ68 ዓመቱ ኦልሜርት ጉቦ በመቀበል በቀረቡባቸው በሁለት የክስ ጭብጦች ከ6 ሳምንታት በፊት የጥፋተኝነት ብይን ተላልፎባቸው ነበር ። ኦልሜርት ላይ ትናንት ውሳኔ የተላለፈው ለሁለት ዓመታት ከተካሄደ የፍርድ ሂደት በኋላ ነው ። ኦልሜርት 160 ሺህ ዶላር የሚደርስ ጉቦ ተቀብለዋል ሲል ፍርድ ቤቱ አስታውቋል ። ርሳቸው ግን ጉቦ አልተቀበልኩም ሲሉ ተከራክረዋል ። ብይኑንም ይግባኝ እንደሚሉ ጠበቆቻቸው አስታውቀዋል ። ይግባኑ በፍርዱ ላይ ለውጥ ካላስከተለ በስተቀር ኦልሜርት በጎርጎሮሳውያኑ መስከረም 1 ፣ 2014 ዓመተ ምህረት ወህኒ ይወርዳሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ኦልሜርት በጉቦ ቅሌት እስር የተበየነባቸው የመጀመሪያው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው ። ስለ ብይኑ የእስራኤል ሃይፋውን ወኪላችንን ግርማው አሻግሬን በስልክ አነጋግረናል ።

ግርማው አሻግሬ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ